Print this page
Saturday, 27 June 2020 12:01

"ወርልድ ቪዥን" ከ1.7 ሚ. ብር በላይ የሚያወጡ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

 ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ከአንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ አይነት የኮረና ቫይረስ መከላከያ መሳሪያዎችን ለጤና ሚኒስቴር ለገሰ፡፡
ድርጅቱ ትናንት በጤና ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ በተከናወነ ስነስርዓት፣ ዕቃዎቹን ለጤና ሚኒስቴር ተወካይ ለአቶ ፍቃዱ ያደታ ባስረከበበት ወቅት የድርጅቱ ዳይሬክተር ሚስተር ኤድዋርድ ብራውን እንደተናገሩት ድርጅቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ፤ የሚገኘውን የኮረና ቫይረስ መከላከልና ህሙማኑን ለማከም የሚያስችሉ የሙቀት መለኪያ፣ ጓንት፣ (የፊት መሸፈኛ ማስክ) እንዲሁም ለኮቪድ 19 ህክምና የሚያገለግሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች መሆናቸውን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ ይህ በወሳኝ ጊዜ ላይ የተደረገና እጅግ አስፈላጊ የሆነ ድጋፍ ነው ብለዋል:: ይህ ድጋፍ ድርጅቱ በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች እያከናወናቸው የሚገኘውን ዘርፈ በዙ ማህበረሰብ አቀፍ ተግባራት አካል እንደሆነም ሚስተር ኤድዋርድ ገልፀዋል፡፡ ድርጅቱ ወደፊትም በሽታውን ለመከላከል በሚያስችሉ ተግባራት ላይ ከማህበረሰቡ ጐን የሚቆም መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ተወካዩ አቶ ፍቃዱ ያደታ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ድጋፎቹ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን አገራዊ ርብርብ በእጅጉ የሚያግዙ እንደሆነና እንዲህ ዓይነት ድጋፎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

Read 1065 times