Print this page
Saturday, 27 June 2020 12:02

የደቡብ ኦሞ ዞን የክልልነት ጥያቄ አቀረበ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

  16 ብሄረሰቦች የያዘው የደቡብ ኦሞ ዞን ራሱን ችሎ ክልል እንዲሆንና ዞኑን በቅርቡ በጥናት በተለየው የኦሞቲክ ክልል ስር ለማካተት የሚደረገው ጥረት ተቀባይነት እንደ ሌለው የዞኑ ም/ቤት አስታወቀ።
የደቡብ ኦሞ ዞን ራሱን የቻለ ክልል እንዲሆን የሕዝብ ፍላጎት መኖሩን በዞኑ ም/ቤ ስብሰባ ወቅት ከተሳታፊዎች በስፋት መንፀባረቁን የስብሰባውን ሂደት የተከታተሉ ምንጮች ለአዲስ አድማስ ያስገነዘቡ ሲሆን በአቶ አባዱላ ገመዳ የሚመራው 83 አባላት ያሉት የሰላም አምባሳደሮች ቡድን ዞኑን አዲስ ይመሰረታል ከተባለው የአሞቲክ ክልል ውስጥ ለማካተት ያስቀመጠው ጥናት ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም የሚል ውሳኔ በም/ቤቱ መተላለፉን ማወቅ ተችሏል።
የሰላም  አምባሳደሮች ቡድኑ በአካባቢው ተገኝቶ ጥናት ሲያደርግ ደቡብ ኦሞ ዞን ራሱን የቻለ ክልል የመሆን ፍላጎት እንዳለው በስፋት የተገለፀለት ቢሆንም የሕዝቡን ፍላጎትና ስሜት ሳይጠብቅ በሌላ ክልል አደረጃጀት ውስጥ እንዲካተት ምክረ ሀሳብ ማቅረቡ የሕዝብን ፍላጎት የደፈጠጠ መሆኑ በም/ቤቱ በስፋት ተንሸራሽሯል።
በጥናቱም የጥቂት ሰዎች አስተሳሰብ እንደተንፀባረቀ ይህንንም በተመለከተ ለጠ/ሚሩ ጽ/ቤት አቤቱታ በሰነድ ቀርቦ ምላሽ እየተጠበቀ መሆኑ ተገልጿል።
የደቡብ ኦሞ ዞንን በአዲሱ የኦሞቲክ ክልል ስር ለማካተት የሚደረገው ጥረትም ፈጽሞ ተቀባይነት እንደሌለው ም/ቤቱ በሙሉ ድምጽ ውሳኔ ማሳለፉም ታውቋል።
በሰላም አምባሳደሮች ኮሚቴ ተጠንቶ በቀረበው የደቡብ ክልልን ቀጣይ እጣ ፈንታ በሚያመለክተው ምክረ ሀሳብ መሰረት ራሱን ችሎ ክልልነቱ ከታወጀው ሲዳማ ክልል በስተቀር የቀሩት በሶስት ክልሎች እንዲዋቀሩ ይመክራል።
የአንዱ ክልል መጠሪያም ኦሞቲክ እንዲባል በጥናቱ የተጠቀሰ ሲሆን ይህ ክልልም 16 ብሄረሰቦችን በውስጡ ከሚይዘው የደቡብ ኦሞ ዞን ጋር የጋሞ፣ ጎፋ፣ ኮንስ፣ ደራሼ፣ ቡርጂ፣ አማሮን አካቶ እንዲመሰረት ምክረ ሀሳቡ ያመላክታል። 

Read 1308 times