Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 July 2012 07:19

“አንድም ሦስትም ናቸው!”

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የአገር ሽማግሌዎች - “እንደው ንጉሥ ሆይ! ጤናዎን ደህና አደሩ?”

ንጉሥ - “ኧረ ደህና ነኝ! እኔን ያሳሰበኝ የእናንተ ጤና ማጣት ነው! ለእናንተ ስል ካገር በወጣሁ ምን     አሳመማችሁ?!”

- (የኢንዶኔዢያ ምሳሌያዊ አነጋገር)

“የእኛ ሰው እንኳን ከኪሱ ከእድሜህ ላይ ቀንሰህ ጠጣም ቢሉት እሺ ነው የሚለው!”

- የአዲስ አበባ አስተናጋጅ

“የተማረ ይጥረበኝ!” አለች ኮብል - ስቶን

“የምናየው ባለቀለም ቴሌቪዥን (Colour TV የምንኖረው ጥቁርና ነጭ (Black and White)”

- ሀገርኛ አባባሎች

***

የቻይናና የሶቪየት ህብረት ወዳጅነት ከመፍረሱ ጥቂት ቀደም ብሎ የሩሲያው ኒኪታ ክሩስቼቭ እና የቻይናው ቹ ኤንላይ ተገናኙ አሉ -     ጥንት፡፡ የምር ስብሰባ ነው አሉ ያደረጉት… ሁለቱ የተመሳሳይ ርዕዮተ-አለም ተከታዮች፡፡

“እንዴት ነህ ወዳጄ ቹ ኤንላይ?” አለ ክሩስቼቭ፡፡

“ደህና ነኝ ወዳጄ ክሩስቼቭ፡፡ እንደው መሰንበቻህን እንዴት ከርመሃል?”

“የህዝባችን ደህንነት የተከበረ ይሁን! እኔ ደህና ነኝ! አንተስ?”

“የህዝባዊት ቻይና ህልውና እስከተጠበቀና ህዝባችን ኮርቶ እስከኖረ ድረስ እኔ ምን እሆናለሁ፡፡ አብዮታችን ለዘለዓለም ይኑር!” ይህንን ህዝባዊ የእግዜር ሰላምታ ከተለዋወጡ  በኋላ፤

“ይገርምሃል ብዙ ከመኖር ብዙ ትማራለህ፡፡ ከጊዜ በኋላ የችግራችንን ሁሉ ምንጩን አወቅሁት!” አለ ክሩስቼቭ - ሩሲያዊው፡፡

“እንዴት? ምን ሆኖ አገኘኸው?”

“እንዲህ እንደምናወራው ቀላል ባይሆንም ነገሩን ግን አውጥቼ አውርጄ ደረስኩበት፡፡ የአገር ጉዳይ ነው!”

“ምን አይነት የአገር ጉዳይ?”

“ላስረዳህ ነው አትቸኩል፡፡ እኔ የከሰል ሻጭ ልጅ ነኝ፣ የወዛደር ልጅ! አንተ ደግሞ የፊውዳል ማንዳሪኖች የገዢዎች ልጅ ነህ!”

“እና ምን ችግር አለው ታዲያ?”

“ችግሩ እዚህ ላይ ነው፡፡ እኔና አንተ ምንም አይነት የጋራ ነገር የለንም፡፡ አንተ የአገረ-ገዢ ፊውዳል ልጅ፣ እኔ የጭቁን ከሰል አምራች ልጅ! ይህ

ማለት ደግሞ ሩሲያና ቻይና የጋራ ነገር የላቸውም ማለት ነው፡፡ የሚለያየንም ጉዳይ ይሄ ነው!”

“አይ ወዳጄ ክሩስቼቭ፤ እኔና አንተ እንኳን የጋራ ነገር ያለን መሆናችንን አትጠራጠር” አለ ቹ ኤንላይ፡፡

“እኮ ምን? ምን አይነት የጋራ ነገር ነው ያለን?”

“ምን መሰለህ አንድ የሚያደርገን?

- አንተም መደብህን ክደሃል!

- እኔም መደቤን ክጃለሁ!”

***

መደባችንን ከመካድ ያድነን፡፡ የአንድ ርዕዮተ-ዓለም አስተናጋጅ፣ የአንድ እምነት ተከታይ ሆነን የተለያየን ነን ከማለት ይሰውረን! ትውልዳችንን መቁጠር ትተን የሆነውን ነገር በግልፅ የምንነጋገርበትን ዘመን ያምጣልን! መሪዎች እንደሚመካከሩ የማያውቅ ህዝብ እንዳንሆን ልቡናውን ይስጠን!

“ንጉሥ ማለት ማን እንደሆነ አሁን ገባህ ወይ?” ብለው ንጉሡ በፈረስ ያፈናጠጡትን ባላገር ቢጠይቁት፤

“እንግዲህ ወይ እርሶ ወይ እኔ ነና!” አለ አሉ፡፡ ከዚህም ይሰውረን፡፡ ህዝባዊ ንጉሥ ነኝ የሚሉ ህዝብ አይደሉም፡፡ ህዝባዊም አይደሉም፡፡ ስለህዝብ ሊናገሩ ይችሉ ዘንድ ስልጣን ሊሰጣቸው ይችላሉ እንጂ! ህዝብም ልባቸውን ሳያውቅ ይወክሉኛል ብሎ ሊገበዝ አይገባውም! ይልቁንም የሀገሩን ሉአላዊነትና የእሱን ጥቅም በተጨባጭ ሊያስጨብጡለት መቻላቸውን ማረጋገጥ ነው የሚጠበቅበት! “ንጉሥ ማለት ሥርዓት ነው” ይላሉ ሩቅ ምሥራቆች፡፡ መሪ፤ ሥርዓቱን በአምሳሉ ይቀርፃል ለማለት ነው፡፡ የሥርዓቱ መዋቅርና የሥርዓቱ መሣሪያዎች (State apparatus and state machinery እንዲሉ) ቢሮክራሲው፣ መከላከያው፣ ደህንነቱ ሁሉ የሀገሪቱን ጥቅም ማስጠበቂያ ይሆኑ ዘንድ የመሪው ፖለቲካዊ፣ ሰብዕናዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጤናማነት ወሳኝ ነው፡፡ ስታሊን “ደንስ!” ብሎ ካዘዘ ትደንሳለህ እንጂ “ለምን?” ብለህ አትጠይቅም” ይላሉ ሩሲያውያን፡፡ ዲሞክራሲ የወደመው ለዛ ነው፡፡ አንድ ሩሲያዊ ፖለቲከኛ ዲፕሎማት “ኢትዮጵያውያን የፑሽኪንን ሐውልት ከወገብ በላይ (Bust) ሰሩ፡፡ ኤርትራውያን ደግሞ በሙሉ ቁመት (Human Size) ሐውልቱን ሰሩ፡፡ ይህ ለምን የሆነ ይመስልዎታል?” ተብለው ሲጠየቁ “ኢትዮጵያውያኑ ከወገቡ በታች አደባባዩ ነው ብለው የሚያምኑ ይመስለኛል፡፡

ኤርትራውያኑ ደግሞ ፑሽኪን ሙሉውን አደባባያችን ነው ብለው ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሩሲያ ሙሉ እምነትና ግማሽ እምነት ያላቸው አገሮች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ሁሌም ይኖራሉ፡፡ ዋናው ነገር ግን አበሾች ሁሉ ፑሽኪን የእኛ ነው ብለው ማመናቸው ነው!” ብለው መለሱ ይባላል፡፡ ጐረቤቶቻችንን ሁሉ ጤና ያድርግልን!

እኛ ኢትዮጵያውያን ባህላዊ ስምምነታችንና ልዩነታችንን ማቻቻላችን ማንም ሳይነግረን ያለን የነበረንና የሚኖር እሴታችን ነው፡፡ ፖለቲከኞቻችን ያንን ሊያጡ ይችላሉ፡፡ ህዝብ ግን ያእሴት ሁሌም አለው፡፡ ለምሳሌ፤ የጊዮርጊስ ቡድን ቀንደኛ ደጋፊ የቡናን ቡድን ቀንደኛ ደጋፊ ምሳ ጋብዞ ሲተራረቡ ይውላሉ፡፡ መንግሥት ግን ስታዲየም ይጣላሉ ብሎ ፖሊስ ይመድባል እንደማለት ነው፡፡ ስለግልፅነት ስናወራ ግልፅ መሆን አለብን፡፡ ስለ ዲሞክራሲ ስናወራ ዲሞክራት መሆን አለበት፡፡ እንደዚሁ ስለ መቻቻል ስናወራ በእርግጥ እንደምንቻቻል እያሳየን ሊሆን ይገባል፡፡ የህዝብን ትእግሥት የህዝብን መቻቻል ፖለቲከኞቻችን ልብ ሊሉ ይገባል፡፡ ህዝብ ደህንነቱን እንዲያስብ ማድረግ እንጂ ለሁሉ ነገር ፖሊስ መድበን አንችለውም፡፡ ይልቁንም ስለ ሉአላዊነቱ፣ ስለ መሪው፣ ስለ አገሩ ፖለቲካ የገባው ህዝብ (Informed Public) ለመፍጠር ብንጥር ነው የሚሻለው፡፡ ዞሮ ዞሮ ባለቤቱ፣ አድራጊ-ፈጣሪው እሱ ነውና!

በዱሮው ዘመን ፊውዳሊዝም፣ ቢሮክሲያዊ ካፒታሊዝም እና ፋሺዝም፣ አንድም ሦስትም ናቸው ይባል ነበር፡፡ ዛሬ ከነዚህ ውስጥ የትኞቹ ቅሪት (reminant) እንዳላቸው ለመገመት ቢያዳግትም ያለጥርጥር ቢሮክራሲውና ካፒታሊዝም ፀሀይ የሞቃቸው አገር የሚያያቸው ሁነቶች ናቸው - የየጉዳያችን ምክንያቶች (raison d’etre እንደሚሉት ፈረንሣዮቹ)፡፡ የእነዚህ መገለጫዎች የመሪዎች አመለካከት ጤና መሆን፤ የኑሮ ውድነት መናርና የምሁራዊ የሰው ኃይል ሥራ-አጥነት አንድም ሦስትም መሆናቸው ነው!!

 

 

Read 4162 times Last modified on Saturday, 14 July 2012 07:23