Print this page
Saturday, 11 July 2020 00:00

የኮሮና ቫይረስ አየር ወለድ በሽታ መሆኑ ተጠቆመ

Written by  መታሰቢያ ካሣዬ
Rate this item
(0 votes)

 • ቫይረሱ በአየር ላይ ለሰዓታት ይቆያል፤ ከ8-9 ሜ. የመጓዝ አቅም አለው
            • ህብረተሰቡ ጠበቅ ያለ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሠሰቢያ ተሰጥቷል።
                  
          ኮሮና ቫይረስ አየር ወለድ በሽታ ነው መባሉ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን ቫይረሱ በአየር ላይ ለሰዓታት ሊቆይ እንደሚችልና  ይህም ከዚህ ቀደም በሽታውን ለመከላከል በሚወሰዱ ጥንቃቄዎች ላይ ለውጥ እንደሚያስከትል ተነግሯል።
የአለም ጤና ድርጅት ሰሞኑን ይፋ ያደረገውና 279 ተመራማሪዎች የተሳተፉበት  ምርምር ውጤት እንደሚጠቁመው  የኮሮና ቫይረስ በአየር ላይ ለሰዓታት  የሚቆይ ሲሆን  ከ8-9 ሜትር ርቀት የመጓዝ አቅም እንዳለውም ታውቋል። ተመራማሪዎቹ ይሄንኑ የምርምር ውጤት ለዓለም ጤና ድርጅት ያቀረቡ ሲሆን ድርጅቱ የምርምር ውጤቱን በመቀበል በበሽታው መካላከያ መንገዶች ላይ ያሉት ነገሮች እንደገና እንደሚያጤነው መግለጹን ዘጋርዲያን ዘግቧል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ  ፣ የውስጥ ደዌና ተላላፊ በሽታዎች ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ወንደሰን አሞኘ እንደሚናገሩት ፤ አሁን በዓለም ጤና ድርጅት ቀረበ የታባለው ሪፖርት ፤  ቀደም ሲልም በበሽታው ላይ ምርምር ሲያደርጉ በነበሩ ተመራማሪዎች ሲነሳ የቆየ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው ይህም ህብረተሰቡ በሽታውን ለመከላከል ሲጠቀምባቸው በነበረባቸው የጥንቃቄ መንገዶች ርቀት  ላይ ተጨማሪ ነገሮችን በማከል እራሱን ከበሽታው እንዲከላከል የሚያደርግ ነው ብለዋል።
የበሽታው ስርጭት በተለይም በተዘጉና  አየር እንደ ልብ በማይንቀሳቀስባቸው ስፍራዎች፣ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ባሉባቸው አካባቢዎችና በህክምና መስጫ ስፍራዎች ላይ ሊጨምር ስለሚችል ህበረተሰቡ በነዚህ ሰስፍራዎች ላይ ተጨማሪ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ባለሙያው አሳስበዋል።
የህብረተሰብ ጤና ባለሞያው እና በኮቪድ 19 መከላከል ኮሚቴ ውስጥ በመስራት ላይ የሚገኙት ዶ/ር ሰሎሞን ወርቁ በበኩላቸው በሽታው በየጊዜው የተለያዩ አዳዲስ ነገሮችን እያመጣ መሆኑንና  ከበሽታው አዲስነትም አንጻር በበሽታው ላይ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች ገና መቋጫ ባለማግኘታቸው ምክንያት በየጊዜው አዳዲስ ነገሮች እየተገኙ ነው። በዚህም መሰረት ከዚህ ቀድሞ በሽታው ከአፍና ከአፍንጫ ውስጥ በሚወጡ እርጥበቶች ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ እንደሆነና  አየር ላይ የመቆየት እድሉም አነስተኛ መሆኑ ሲነገር ቆይቷል።  አሁን ተመራማሪዎቹ በሽታው አየር ወለድ መሆኑን እና አየር ላይ የመቆየት ዕድል እንዳለው መግለፃቸው በሽታው መከላከል ተጨማሪ ጠበቅ ያሉ ጥንቃቄዎች ማድረግ እንደሚገባ አመልካች ነው ብለዋል። በሽታውን በማከም ላይ የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ቀደም ሲል ከነበረው የበለጠ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የገለፁት ዶ/ር ሰሎሞን ህበረተሰቡም የሚጠቀምባቸውን የአፍና የአፍንጫ መሸፈናኛ ማስኮች በአግባቡ ሁል ግዜም ሊጠቀም እንደሚገባ እና የሚጠቀማቸው ማስኮችም የተሻሉ እንዲሆኑ መክረዋል።


Read 1961 times