Print this page
Saturday, 18 July 2020 15:40

በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የምግብ እጥረት መከሰቱ ተጠቆመ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

  በአሁኑ ወቅት በመካከለኛና ምስራቅ ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በግጭት፣ በኮሮና ወረርሽኝ፣ በድርቅ፣ በእህል ዋጋ መጨመርና በበረሀ አንበጣ ጥቃት የተነሳ የምግብ እጥረት መከሰቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከሰሞኑ ባወጣው ሪፖርት  አስታውቋል፡፡
በተለይ በሰሜንና በመካከለኛ አማራ ክልል በዋነኝነት ዋግኸምራ አካባቢ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂ፣ አርሲና የቦረና ቆላማ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ የምግብ እጥረት መከሰቱን ጠቁሟል፤ ሪፖርቱ:: ለእጥረቱ መከሰት ዋነኛ ምክንያቶች ተብለው ከተጠቀሱት መካከልም፡-የበልግ አዝመራ ወቅት እንደተጠበቀው አለመሆን፣ ሰብሎች በበረሀ አንበጣ መውደማቸው፣ በአካባቢው ከዚህ በፊት የነበረ ድርቅ እንዲሁም በየጊዜው የሚፈጠሩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ይገኙባቸዋል፡፡
በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የክረምቱ ዝናም ከሚፈለገው በታች እንደሚሆን የተነበየው ሪፖርቱ፤በቀጣይ እንስሳትም ጭምር በድርቁ ሊጎዱ ይችላሉ ብሏል፡፡ መንግስት ለአካባቢዎቹ ትኩረት ሰጥቶ ዜጎች የምግብ አቅርቦት ከወዲሁ የሚያገኙበትን መንገድ እንዲፈጥር ያሳሰበው ሪፖርቱ፤ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች እርዳታ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል ፡፡


Read 10363 times