Saturday, 18 July 2020 16:38

“የቆረኑ ጉዞ” ልቦለድ መፅሃፍ ወጣ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በደራሲና ጋዜጠኛ ወይንሸት በየነ ዘውዴ የተሰናዳውና በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው “የቆረኑ ጉዞ” ልቦለድ መፅሃፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ መጽሐፉ መቼቱን ከአዲስ አበባ 245 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የሰሜን ሸዋዋ “ራሳ” ላይ ያደረገ ሲሆን፤ በዋናነት በአፋርና በአማራ ክልል ባለማወቅና በአጉል ልማድ ወንድም አማች ህዝቦች እየተገዳደሉ የቀጠሉበትን ሂደት ይዳስሳል።
ጋዜጠኛ ወይንሸት በየነ ከገፀ ባህሪያቱ በላይ በዚህ አካባቢ ኖራ የሁለቱ ብሔሮች የዘወትር ግጭትና ደም መፋሰስ እያሳሰባትና ጥያቄ እንደሆነባት በማደጓ አሁን ይህ አጉል ልማድ ቀርቶ ሰላም እንዲፈጠር በሚል የሁለቱን ብሔሮች ታሪካዊ ሂደት ገፀ ባህሪያትን አላብሳ እነሆ ስለማለቷ በመጽሐፉ መግቢያ አስፍራለች በ206 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ101 ብር ከ50 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል። ጋዜጠኛዋ ከዚህ ቀደም “ተቀባይ የሌለው መልዕክት እና ሌሎችም አጫጭር ልቦለዶች እና “ምሳሌያዊ አነጋገር ስነፍቻዊ ፋይዳና አንድምታ” የተሰኙ መጽሐፎችን ለንባብ ማብቃቷ አይዘነጋም።

Read 18676 times