Print this page
Saturday, 18 July 2020 16:14

“ዜና ኢትዮጵያ 1 እና 2” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በመምህር ቆሞስ አባ ክንፈ ገብርኤል ገ/ኢየሱስ የተሰናዳውና የኢትዮጵያን አንድነትና ታሪክ ትውልዱ አንብቦ ከተሳሳተ መንገድ እንዲመለስ ይረዳል የተባለው ዜና ኢትዮጵያ 1 እና 2 መጽሐፍ ለንባብ በቃ።
መጽሐፉ ትውልዱ ታሪኩን አንብቦ እንዲኮራ ሀገሩ ኢትዮጵያ ማን እንደሆነች እንዲረዳ አንድነቱንና ወንድማማችነቱን በማጥበቅ ከእርስ በርስ ጥላቻና መተላለቅ እንዲሁም ከመገፋፋት ተቆጥቦ በአገሩና በሀይማኖቱ የማይደራደር እንዲሆን የሚያሳስብም ነው። “ሀገር ማለት ምግብ፣ ለተጠማው የደስታ ወይን፣ ለታረዘው የጽድቅ መጐናፀፊያ፣ መጠጊያ ላጣው መጠጊያ በመሆኗ ይህችን አገር ለማወቅ ትውልድ ታሪኩን ማወቅና መኩራት አለበት” በማለት መጽሐፉን ማሰናዳታቸውን መምህር ቆሞስ አባ ክንፈ ገብርኤል ገ/ኢየሱስ በመግቢያቸው አስፍረዋል።
ታሪክን ከሀይማኖት እያሰናሰለ የሚተርከው መጽሐፉ በ514 ገጽ ተመጥኖ በ250 ብር ለገበያ ቀርቧል።   

Read 1237 times