Saturday, 25 July 2020 14:59

አቶ ልደቱ አያሌው በቁጥጥር ሥር ዋሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

    ሁከት በማስነሳትና በገንዘብ በመደገፍ ተጠርጥረዋል

             የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) መስራችና አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው፤ ሁከትና ረብሻ በማስነሳት ተጠርጥረው በኦሮሚያ ፖሊስ መታሰራቸው ታውቋል፡፡
ትናንት ረፋድ 4 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ በፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ልደቱ፤ ወዲያው መኖሪያ አድራሻቸው ወደሚገኝበት ወደ ቢሾፍቱ መወሰዳቸውን የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያን ተከትሎ በቢሾፍቱ ከተማ የተቀሰቀሰውን ሁከትና ብጥብጥ በማስተባበርና በገንዘብ በመደገፍ ተጠርጥረው መያዛቸውን አቶ አዳነ ተናግረዋል::
አቶ ልደቱን የከሰሳቸው የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንደሆነና ጉዳያቸውም በቢሾፍቱ ወረዳ ፍ/ቤት የሚታይ መሆኑን አቶ አዳነ ከክስ መጥሪያው መረዳት መቻሉን አስረድተዋል፡፡


Read 7240 times