Saturday, 25 July 2020 15:53

ወላዶች በጤና ተቋማት እንዲወልዱ ይበረታታሉ፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

  ‹‹….በእድሜዬ የሰባ አመት እናት ነኝ፡፡ እኔ የሁለት ሴት እና የሁለት ወንዶች ልጆች እናት ነኝ:: ….ታዲያ ምን ገጠመኝ መሰላችሁ…. የአንዱ ልጄ ሚስት እርጉዝ ነበረች፡፡ ልጅትዋ ከመውለድዋ በፊት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ካልተቸገራችሁ በስተቀር ከቤታችሁ ቆዩ የሚል ማሳሰቢያ በኢትዮጵያ መንግስት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አማካኝነት ከሌሎች የመከላከያ ዘዴዎች ጋር በየቀኑ ይነገር ነበር:: ግንኙነቱ እና ስራው በከፊልም ቢሆን በስልክ ሆነ፡፡
ታዲያ አንድ ቀን ምን ሆነ መሰላችሁ….ልጄ በድንገት ከምሽቱ አራት ሰአት ላይ ይደውል ልኛል:: እኔም …..ሄሎ….ስል …..እማዬ….እማዬ…ድረሽልኝ…ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡ እኔም በምሽት መኪናዬን አስነስቼ እየበረርኩ ከልጄ ቤት ደረስኩ:: ….ቤቱ በጭንቅ ተይዞአል፡፡ ….ምንድነው ጉዱ …አልኩ:: የልጄ ሚስት እናት ኮሮና በአገር ደረጃ መኖሩ ስለተነገረ እና በይበልጥ ደግሞ በየሆስፒታሉ እና ጤና ጣቢያው ቫይረሱ ሊተላለፍ ስለሚችል ልጄ ወደዚያ አትሄድም…ከቤት መውለድ አለባት:: እኔ ማዋለድ የሚያውቁ ሴት አመጣለሁ…እናንተ ግን ከቤት እንዳትወጡ የሚል ትእዛዝ ሰጥተው ሄደዋል …ተባልኩ….፡፡ ልጅትዋ በምጥ ተይ ዛለች:: ባለቤትዋ(ልጄ) በጭንቀት ከወዲያ ወዲህ ይላል::….አንተ መኪናህን አስነስተህ ወደ ሆስፒታል አትወስዳትም እንዴ….ስለው… ልጄን ከቤት ይዘህ እንዳትወጣ ብለው ስላስጠነቀቁኝ ፈራሁ ይለኛል:: እኔም …ልጅቱን ተነሽ እንሂድ ስላት…እሺ እማማ…አለችኝ…እኔም አማቼ ሳይመጡ ልጅቱን ይዤ ወደጤና ተቋም በረርኩ፡፡ ጤና ጣብያው በተገቢው ሁኔታ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ልጃችንን ሴት ልጅ አሳቀፈልን፡፡ የልጅትዋ እናት ግን እስከአሁን በድርበብ ነው የሚያ ናግሩኝ፡፡ ለመሆኑ ኮሮና ቢመጣ …ተገቢው ጥንቃቄ ተደርጎ እናቶች በጤና ተቋም ይወልዳሉ እንጂ በስንት መከራ የተሻሻለውን እና በቤት መውለድ የቀረውን እንደገና ወደሁዋላ ለመመለስ ሰው እንዴት ይታገላል? በሆስፒታሉም ካሉ ባሙያዎች የሰማሁት በተለይም የእር ግዝና ክት ትል የሚያደርጉት እናቶች ቁጥር እንደቀነሰና እነሱ ግን አገልግሎቱን ለመስጠት ምንጊዜም ዝግጁ መሆናቸውን ነው፡፡ እናም…እባካችሁ እናቶች…ልጆቻችሁ…በቤት ሳይሆን ወደ ጤና ተቋም ሄደው ልጃቸውን እንዲወልዱ እርዱአቸው፡፡›››
ዝናሽ ባንተይርጋ …ከወሰን
ወ/ሮ ዝናሽ እንደገለጹት ብዙ ሴቶች ልጆቻቸውን ከቤት ሆነው ለመውለድ ወሰነው ያድርጉት አያድርጉት ወደፊት በጥናት የሚረጋገጥ ሲሆን አነዳንዶች ግን እንደሚያደርጉት ይነገራል፡፡ የደረ ሰንን መልእክት መሰረት በማድረግ ወደዩኒሴፍ ድረገጽ አምርተናል፡፡ በገጹ ፌቨን ጌታቸው አንድ እውነታ አስነብባለች፡፡ ፌቨን ያስተናገደቻትን ወጣት እናት እና የሕክምና ባለሙያ እኛ በአካል ስላላገኘናቸው ለጊዜው ስማቸውንና ምስላቸውን መጠቀሙን ትተነዋል፡፡
COVID-19
By Feven Getachew
ይህ ቀን የ21 አመት እድሜ ላላት ወጣት የተለየ ቀን ነው፡፡ ወጣትዋ የመጀመሪያ ልጅዋን በአዲስ አበባ ልደታ ጤና ጣቢያ በሰላም ተገላግላለች፡፡ እንደወላድዋ ምስክርነት በ COVID-19 ምክንያት ደስታዋ ላይ ዳመና ያንዣበበበት እና መወሰን የሚገባትን ነገር በሚመለከት ጭንቀት ውስጥ የገባችበት ነበር፡፡ ወጣትዋ ካረገዘች ጊዜ ጀምሮ የምትሻው በጤና ተቋም እንድትወልድ ሲሆን ነገር ግን ሀሳብዋን ማንም ሊደግፋት አልቻለም ነበር፡፡ ምስክርነትዋን እንደሚከተለው ገልጻለች፡፡
‹‹…ጎረቤቶቼ እንዲህ ነበር ያሉኝ፡፡ ….በጭራሽ ወደ ጤና ተቋም እንዳትሄጂ…ለመውለድ ብለሽ ከዚያ ብትሄጂ በኮሮና ቫይረስ ትያዣለሽ…የሚል .ነበር ንግግራቸው፡፡ ይልቁንስ…አሉ ጎረቤ ቶች…ከቤትሽ ብትወልጂ የኮሮና ቫይረስም ሳይይዝሽ በሰላም ልጅሽን ታቅፊያለሽ የሚል ነበር ምክራቸው፡፡ ››
የኮሮና ቫይረስ ባይኖር ኖሮ ወጣትዋ በመውለድዋ ምክንያት ብዙዎች በደስታ በዙሪያዋ ይገኙ ነበር፡፡ ነገር ግን የኮሮና ቫይረስን በመፍራት ምክንያት መቅረት ከማይችሉት ሰዎች በስተቀር ከዘመድ አዝማዱ በአጠገብዋ ማንም የለም፡፡ በእርግጥ እንደወጣትዋ እማኝነት ሰዎች በዙሪያዋ ባለመሰብሰባቸው የተሰማት ሀዘን ከጊዜው ጋር በተያያዘ እንጂ በሰዎች ላይ ያተኮረ አይደለም::  ምክንያቱም ሁሉም ሰው በርቀት ሆኖ እራሱን ከቫይረሱ መከላከል እንደሚገባው እና ለእሱዋም ችግር እንዳይሆን ስለምታምን ነው፡፡ በቀጥታ የተናገረችው የሚከተለውን ነው፡፡
 “I am sad that my families are not able to visit me to see my first born,” ……says.  
‹‹…የመጀመሪያ ልጄን ወልጄ …ነገር ግን ቤተሰቦቼ ሊጎበኙኝ መምጣት ባለመቻላቸው አዝኛለሁ..›› ነበር ያለችው፡፡
ፌቨን ጌታቸው በልደታ ያለውን ጤና ጣቢያ አሰራር በተመለከተችበት ወቅት የጤና ባለሙያም አነጋግራለች፡፡ ባለሙያዋ የሚከተለውን ምስክርነት ነበር የሰጠችው፡፡
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ቫይረሱ መከሰቱን ለህዝብ ይፋ ካደረገችበት እ.ኤ.አ ከማርች 16/ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በየጊዜው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣት ላይ መሆኑን በየጊዜው የሚቀርቡ ሪፖርቶች ይገልጻሉ፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ቫይረሱ በአገር ውስጥ መከሰቱ ሪፖርት ከተደረገበት ወቅት ጀምሮ ግን ታካሚዎች ወደጤና ተቋሙ ለመምጣት የፈሩበት ሁኔታ ታይቶአል፡፡ በየጊዜው እንዳየነው ከሆነ ታካሚዎች ቁጥራቸው በጣም ቀንሶ ነበር፡፡ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ የተገነዘቡት ነገር ይበልጡኑ በኮሮና ቫይረስ የመያዝ እድል በጤና ተቋም ይበዛል የሚል ነበር፡፡
እነዚህን ፍርሀቶች ለማስወገድም የጤና ተቋማቱ ታካሚዎች ከቫይረሱ እራሳቸውን የሚጠብቁባ ቸውን የመከላከያ ዘዴዎች ማለትም እጅን ለመታጠብ የሚያስችሉ ዝግጅቶች፤የሙቀት መለኪያ አገልግሎትን በመግቢያው ላይ እንዲሰጥ እና ለሕክምናው በሚገቡበትም ሆነ ተራ በሚጠብቁ በት ክፍል ተራርቀው እንዲቀመጡ የሚያስችሉ ዝግጅቶችን በማድረግ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረ ዋል፡፡ የጤና ባለሙያዋ የሚከተለውን እውነታም ተናግረዋል፡፡ ‹‹… በእርግዝና ላይ ላሉ እና አገልግሎቱን ለሚፈልጉ እናቶች በሙሉ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸ ውን ለማወቅ የሚያስችል ዝግጅት እና ምርመራ በማድረግ ከእርግዝና በፊት፤በእርግዝና ጊዜ እና፤በወሊድ ወቅት ሙሉ ደህንነታቸውን መጠበቅ የሚያስችል አቅም መኖሩን አስረድተና ቸዋል:: በየጊዜውም እያስረዳናቸው ነው፡፡ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችም እናቶቹን ቤት ለቤት በመጎብኘት፤ስልክ በመደወል ያላሰለሰ ክትትል በማድረግ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡››
እንደ ኤ.ኤ 2019/ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት እንደታየው ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ የእና ቶችን እና የህጻናትን ሞት በመቀነስ ረገድ ለውጥ ካስመዘገቡት አገሮች መካከል ነች፡፡ነገር ግን የኮሮና ቫይረስ በፈጠረው ፍርሀት በጤና ተቋማቱ መገልገል ከቀነሰ የሚጎዱ እናቶችና ህጻናት ቁጥር እንዳይጨምር ያሰጋል፡፡ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው የኮሮና ቫይረስ ከመከሰቱ ስምንት ወር በፊት ከነበረው የህጻናት የህክምና አገልግሎት ወደ 9% ቀንሶ መገኘቱ ተመዝግቦአል፡፡ የዚህም ምክንያት ወላጆች ልጆቻቸውን ወደህክምና ተቋም ከመውሰድ በመቆጠ ባቸው ምክንያት ነው …ዩኒሴፍ እንደገለጸው፡፡
ፌቨን ጌታቸው በዩኒሴፍ ድረገጽ ያሰፈረቻት ባለሙያ በስተመጨረሻውም እንዳረጋገጠችው…. ‹‹…ወላጆች ምንም እንኩዋን ወደጤና ተቋም ለመምጣት ፍርሀት ቢሰማቸውም የጤና ተቋሙ ግን ፍርሀቱ አግባብ አለመሆኑን ተገልጋዮች ሊያውቁ የሚችሉባቸውን መንገዶች እያሳየ ነው፡፡ ለም ሳሌም አፍና አፍንጫን መሸፈን፤ አገልግሎቱን ለማግኘት ተራርቆ መቀመጥ፤ተራ በመጠበ ቂያ ቦታዎች የሰዎችን ቁጥር መወሰን፤እጅን በሚገባ መታጠብ…የመሳሰሉትን የጥንቃቄ ተግባራት በመፈጸም ወላጆችም ሆኑ ወላዶች ለደህንነታቸው እምነት እንዲኖራቸው አስፈላጊው ተግባር እየተፈጸመ ነው…›› ብላለች፡፡  
COVID-19
By Feven Getachew



Read 11411 times