Print this page
Saturday, 25 July 2020 16:03

የጄፍ ቤዞስ ሃብት ሰኞ ዕለት ብቻ በ13 ቢ. ዶላር ጨምሯል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

    በእንግሊዝ የጊታር ሽያጭ 80 በመቶ አድጓል

               የአለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነር እና የአማዞን ኩባንያ መስራች የሆኑት አሜሪካዊው ጄፍ ቤዞስ፣ ባለፈው ሰኞ ብቻ ተጨማሪ 13 ቢሊዮን ዶላር ሃብት ማፍራታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የተጣራ ሃብታቸው 189 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡
ቢሊየነሩ ከፍተኛውን የአንድ ቀን ተጨማሪ ሃብት ያፈሩት በኢንተርኔት ግብይት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ገዢዎች ያሉበት ድረስ የሚያደርሰው ኩባንያቸው አማዞን፤ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በመላው አለም ከቤታቸው የማይወጡና በአማዞን በኩል ግዢ የሚፈጽሙ ሰዎች ቁጥር ከመበራከቱ ጋር በተያያዘ የኩባንያው የአክሲዮን ዋጋ ክብረወሰን ያስመዘገበ የ8 በመቶ ዕድገት በማሳየቱ ነው ተብሏል፡፡
በሌላ የቢዝነስ ዜና፣ በእንግሊዝ የኮሮና ቫይረስ የእንቅስቃሴ ገደቦች በመጣላቸውና ከቤት የማይወጡ ሰዎች ቁጥር ከመበራከቱ ጋር ተያይዞ በቤታቸው ሆነው ሙዚቃ የሚጫወቱና በኢንተርኔት የሚያሰራጩ ዜጎች ቁጥር መጨመሩንና በአገሪቱ የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በአገሪቱ ታዋቂ የሆኑ የሙዚቃ መሳሪያዎች ሻጭ ኩባንያዎችን ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ እስከ ሰኔ በነበሩት ሶስት ወራት በአገሪቱ የጊታር ሽያጭ በ80 በመቶ ያህል ዕድገት በማሳየት 21.2 ሚሊዮን ፓውንድ የደረሰ ሲሆን የዲጂታል ፒያኖ እና ሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎች ሽያጭም ጭማሪ አሳይቷል፡፡


Read 2325 times
Administrator

Latest from Administrator