Print this page
Wednesday, 29 July 2020 10:15

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከ100 ስመ ጥር አፍሪካውያን አንዱ ሆነው ተመረጡ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ሁለት ሌሎች ኢትዮጵያውያንም በዝርዝሩ ተካትተዋል
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ2020 ዓ.ም 100 ስመ ጥር አፍሪካውያን መካከል አንዱ ሆነው ተመረጡ፡፡
#ሪፒዩቴሽን ፖል ኢንተርናሽናል; የተባለው ተቋም፣ በፈረንጆቹ 2020 በተለያዩ የሙያ መስኮች ስመ ጥር የሆኑ 100 አፍሪካውያንን ዝርዝር ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም በመሪዎች ዘርፍ ከተመረጡት አንዱ ሆነው ተካትተዋል፡፡
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ፣ የላይቤሪያው ምክትል ፕሬዚዳንት ጀዌል ሃዋርድ፣ የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሃፊዝ ጋነምን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ አፍሪካውያንም በዝርዝሩ ውስጥ ተካትተዋል፡፡
ኢትዮጵያዊው #የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ግብ ማዕከል; ዋና ዳይሬክተር  የሆኑት አቶ በላይ በጋሻውም ከ100 ስመ ጥር አፍሪካውያን  አንዱ ሆነው የተመረጡ ሲሆን  ስራ ፈጣሪዋና የሶል ሬብልስ መሥራች  ወ/ሮ ቤተልሄም ጥላሁንም በቢዝነስ የስራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ተመርጠዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም፤ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ደራሲያን፣ የኢኮኖሚ ባለሙያዎችና የስራ እድል ፈጣሪዎችን ጨምሮ በበርካታ የሙያ ዘርፎች ውስጥ የተሰማሩ አፍሪካውያን  በዝርዝሩ ውስጥ ተካትተዋል፡፡
#ሪፒዩቴሽን ፖል ኢንተርናሽናል; ታታሪነት፣ ግልጽነትና ተፅዕኖ ፈጣሪነትን በ100 ስመ ጥር አፍሪካውያን ዝርዝር ውስጥ ለማካተት በመስፈርትነት መጠቀሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 6171 times
Administrator

Latest from Administrator