Saturday, 01 August 2020 13:09

“ቡቃያው” ትርጉም መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ከጣሊያናዊ መሀንዲስ አባትና ከፈረንሳዊት እናት እ.ኤ.አ ሚያዚያ 2 ቀን 1840 ዓ.ም በፓሪስ በተወለደው ኤሚሊ ዞላ “Germinal” በሚል የተፃፈውና ለደራሲው ከ20 መጽሐፎቹ አንዱ የሆነው “ቡቃያው” በሚል በሙሉብርሃን ታሪኩ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል፡፡ መጽሐፉ እንደሌሎቹ የደራሲው ስራዎች በአንድ ዘውግ የተፃፈ አለመሆኑን፣ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ለሁሉም አንባቢ በሚመጥን መልኩ የተዘጋጀ መሆኑንና፤ ደራሲው ኤሚሊ ዞላ የዚህን መጽሐፍ ርዕስ ለመሰየም 23 የተለያዩ ርዕሶችን መርጦ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም “ቡቃያ” የሚል አንድምታ ባለው ቃል “Germinal” ብሎ መሰየሙ ታውቋል፡፡ ይህን ርዕሰ የመረጠበትም ላብ አደሮችን ከዘመናት የጭቆና ቀንበር የሚያላቅቅ አዲስ የሰው ዘር መብቀሉን ለመጠቆም በማሰብ እንደሆነ ተርጓሚው ስለመጽሐፉ ማብራሪያ በሰጡበት የመግቢያ ገጽ ላይ አስቀምጠዋል፡፡
በ420 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ200 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን፤ ዩኒቲ መጽሐፍት መደብር ሲያሳትመው ጃዕፈር መጽሐፍት መደብር በዋናነት እያከፋፈለው እንደሆነ ታውቋል፡፡

Read 11055 times