Thursday, 06 August 2020 18:39

በቤሩት ፍንዳታ አንድ ኢትዮጵያዊ ሲሞት፤ 10 ተጐድተዋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

በሊባኖስ ቤሩት በተከሰተውና ከ135 በላይ ሰዎችን ለሞት፣ ከ5ሺህ በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ለቁስለት በዳረገው የፍንዳታ አደጋ፤አንድ ኢትዮጵያዊ ሲሞት፣ አስር በሚሆኑት ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
ቆንጽላ ጽ/ቤቱ ባሠራጨው መረጃ፤በቤሩት የተለያዩ አካባቢዎች በቤት ሠራተኝነት ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ 10 ኢትዮጵያውያን ላይ ጉዳት መድረሱን ጠቁሟል፡፡ ከተጎጂዎቹ 10 ኢትዮጵያውያን መካከል 8ቱ መጠነኛ ጉዳት፣ሁለቱ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ በዚህ ፍንዳታ ለሞት መዳረጉንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን ቆንጽላ ጽ/ቤቱ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
በቤሩት እስካሁን ምንነቱ በውል ባልታወቀ ፍንዳታ ከ135 በላይ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ ከ5ሺህ በላይ መቁሰላቸውም ታውቋል፡፡ የሀገሪቱ ዜጐች ለፍንዳታው መንግስታቸውን በዋናነት ተጠያቂ ማድረጋቸውን የቢቢሲ ዘገባ ይጠቁማል፡፡ ፍንዳታው የደረሰው ባለፈው ማክሰኞ እንደነበር ይታወቃል፡፡

Read 4043 times