Wednesday, 12 August 2020 00:00

ራፐር ካይኔ ዌስት ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ተዘጋጅቷል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ታዋቂው አሜሪካዊ ራፐር ካይኔ ዌስት በቀጣዩ የአገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በግሉ ለመወዳደር መወሰኑንና ባለፈው ማክሰኞ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ መጀመሩን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ራፐሩ ዊስከንሲንን ወክሎ በምርጫው ለመወዳደር ለግዛቲቱ የምርጫ ኮሚሽን ማመልከቻ ማስገባቱንና ለመወዳደር የሚያስችለውን የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብ መጀመሩን የጠቆመው ዘገባው፣ ከዚህ በፊት የሪፐብሊካኑ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ የነበረው ዌስት በቅርቡ ግን ትራምፕን በአደባባይ መተቸቱንና በምርጫው ለመወዳደር መወሰኑን ይፋ ማድረጉን አስታውሷል፡፡የምርጫ ኮሚሽኑ የድጋፍ ፊርማውን ከቀናት በኋላ ተቀብሎ በመቁጠርና በመገምገም ራፐሩ በምርጫው መወዳደር መቻልና አለመቻሉን በተመለከተ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡
 


Read 5475 times