በወጣቷ ገጣሚ ሳራ ሞገስ የተገጠሙ በርካታ ግጥሞችን የያዘው “ሰካራም ስንኞች” የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ዋለ፡፡ ስለ ተፈጥሮና ነገረሰብ በስፋት የሚዳሰሱ ግጥሞችን የያዘው የግጥም መጽሐፉ፣ ራሳችንን አካባቢያችንና ተፈጥሮን በውሉ እንድናስተውል፣ እንድንቃኝና እንድንገነዘብ ዕድል ይሰጣልም ተብሏል፡፡
አጠርም ረዘምም ያሉ ከ65 በላይ ግጥሞችን ያካተተው መጽሐፉ፣ በ69 ገጽ ተቀንብቦ በ100 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡