Print this page
Saturday, 15 August 2020 14:25

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች "ኮሮና ሊኖርባችሁ ይችላል" በሚል በየመን ጥቃት ተፈጸመባቸው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

     40 ኢትዮጵያውያን በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል

              በየመን በሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን #ኮሮና ሊኖርባቸው ይችላል; በሚል በሁቲ አማፂያን የግድያና የማሳደድ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው የምርመራ ሪፖርቱ አስረድቷል፡፡
አማፂያኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተጠልለውበት የነበረውን አል ጋር የሚባል ሥፍራ ከበው የሃይል ጥቃት እንደሰነዘሩባቸውና በርካቶች በጥይት ተደብድበው እንደሞቱ ሪፖርቱ አመልክቷል:: ድርጊቱ የተፈፀመው ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ መሆኑን ያወሳው ሪፖርቱ፤ ስደተኞቹን #የኮሮና ቫይረስ ሊኖርባችሁ ይችላል; በሚል በጭነት መኪና አሳፍረው ወደ ሳኡዲ ድንበር እንደወሰዷቸውና ሊያመልጡ የሞከሩትን 40 ያህል ኢትዮጵያውያን እንደገደሏቸው ጠቁሟል::  
ሂውማን ራይትስ ዎች ያነጋገራቸው ከጥቃቱ የተረፉ 19 ሰዎችም፤ ኢትዮጵያውያኑ በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ መመልከታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ስደተኞቹ ይኖሩባቸው የነበሩ ከ300 በላይ መጠለያዎች መውደማቸውንም ሂውማን ራይትስ ዎች ማረጋገጡን አስታውቋል:: የሁቲ አማፂያን መሪዎች፤ ኢትዮጵያውያኑ ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ጥቃት ገምግመው ተገቢውን ቅጣት እንዲያስተላልፉ አምነስቲ አሳስቧል፡፡  



Read 5790 times