በኢህአፓ አባሏ አምባሳደር ታደለች ኃይለሚካኤል የተፃፈውና በአምባሳደሯ የልጅነት፣ የኢህአፓ የትግል ጉዞና በኢህአፓ መስራቹ የትዳር አጋራቸው ብርሃነ መስቀል ገዳ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው “ዳኛው ማን ነው” መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ የባልና ሚስቱን የኢህአፓ ትግልና ሂደት አምባሳደሯ ከልጅነት እስከ እውቀት ያሳለፏቸውን የህይወት ኡደቶች በስፋት እንደሚተነትን ታውቋል፡፡
በ442 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ፣ በ295 ብር እና በ24.5 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡