Monday, 17 August 2020 00:00

የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ “ታሪክ አገርና ህገመንግስት” መፅሐፍ ለአንባቢያን ቀርቧል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

አንጋፋው ፖለቲከኛና የታሪክ ምሁሩ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በመጨረሻው የህይወት ዘመናቸው የፃፉት “ታሪክ፣ አገርና ህገመንግስት” የተሰኘው መጽሐፋቸው ታትሞ ሰሞኑን ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡
በመጽሐፉ የመግቢያ ምዕራፍ በባለቤታቸው የሰፈረው ማስታወሻ፤ መጽሐፉ የተዘጋጀው ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከማለፋቸው ከጥቂት ወራት በፊት በ75ኛ ዓመት ዕድሜያቸው ላይ ሳሉ መሆኑን ይጠቁማል፡፡
በአብርሆት ለኢትዮጵያ አሣታሚ ድርጅት የታተመው መጽሐፉ ፣ ታሪክን የሀገር መንግስት ግንባታ እና ህገመንግስትን በትንታኔ የሚዳስስ ሲሆን በ131 ብር ከ70 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡
የታሪክ ምሁሩና ፖለቲከኛው ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በሚያዚያ 2011 ዓ.ም ባደረባቸው ህመም ምክንያት  ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል፡፡


Read 12717 times