Print this page
Tuesday, 18 August 2020 16:44

በኦሮሚያ ክልል የተጠራው ሰልፍ መክሸፉ ተገለፀ

Written by 
Rate this item
(6 votes)

በኦሮሚያ ክልል በሁሉም አካባቢዎች በፀረ ሰላም ሀይሎች ተጠርቶ የነበረው ሰልፍና አድማ በህዝቡና በፀጥታ አካላት ተሳትፎ መክሸፉን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።
የአሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ፤ በውስጥና በውጭ ፀረ ሰላም ሀይሎች የሚደረገው የአድማ ጥሪና የኦሮሚያ ክልልን  የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል የማድረግ ሙከራ የዛሬውን ጨምሮ ለአምስተኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፤ የአድማ ጥሪው፣ ሰላም ወዳድ በሆነው ህዝብና በጸጥታ አካላት የጋራ ቅንጅት ከሽፏል ብለዋል፡፡
ህዝቡ አሁን ያለውን የመልማት፣ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ የሚፈታለትን እንጂ መንገድ የመዝጋት፣ የንግድ እንቅስቃሴን የማቋረጥና መሰል ፀረ ሰላም ድርጊቶችን እንደማይቀበል በዛሬው ዕለት በተግባር አሳይቷል ብሏል፤ ኃላፊው፡፡
ማንኛውንም የአድማ ጥሪ ተከተሎ የኦሮሚያ ክልልን የጥፋትና የሁከት ማዕከል ለማድረግ ከእንግዲህ በኋላ የሚካሄድ ሰልፍ እንደማይኖርም ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ማንኛውም ሰው ከህግ በታች መሆኑንና ላጠፋውም ጥፋት በህጉ መሰረት የሚጠየቅ መሆኑን በመግለፅ፤ ይህንን ለመቀልበስ የሚደረግ ማንኛውም ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ተቀባይነት እንደሌለው አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።
በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ህዝቡን ሰልፍ ለማስወጣት፣ #በእስር ላይ የሚገኘው ጃዋር መሃመድ ሞቷል; የሚል ሃሰተኛ መረጃ ተሰራጭቶ እንደነበር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡



Read 10627 times
Administrator

Latest from Administrator