Saturday, 22 August 2020 00:00

አገር አቀፍ የብሔራዊ መግባባት ውይይት ዛሬ ይጀመራል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል

             ገዥው ፓርቲን ጨምሮ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚሳተፉበት የብሔራዊ መግባባት ውይይት ዛሬ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ አዳራሽ እንደሚጀመር ታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በጽ/ቤታቸው ጠርተው ስብሰባ ባደረጉበት ወቅት በቀጣይ በብሔራዊ መግባባት ላይ ውይይት እንደሚደረግ መጠቆማቸው የሚታወስ ሲሆን የውይይት መድረኩንም የሚያቀናጅ ኮሚቴ ተመርጦ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ እንደሚሳተፉበት የተነገረለት የመጀመሪያው የውይይት መድረክ ዛሬ ይጀመራል ተብሏል፡፡
በኮቪድ -19 ምክንያት በዛሬው ውይይት እያንዳንዱ ፓርቲ በአንድ ሰው የሚወከል ሲሆን በዋናነትም ለብሔራዊ መግባባት ተመርጠው በተዘጋጁ አጀንዳዎች ቅደም ተከተል ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዚህ መድረክ  7 ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች ለውይይት መዘጋጀታቸውም ታውቋል፡፡
ከተመረጡት 7 ዋነኛ የውይይቱ ትኩረቶች መካከልም የሀገሪቱ ታሪክና የአገር መንግስት ግንባታ ሂደት ይገኙበታል ተብሏል፡፡
በዛሬው ዕለት የሚጀምረው የብሔራዊ መግባባት ውይይት መድረክ ቀጣይነት እንደሚኖረውም ታውቋል፡፡   
አንጋፋ የፖለቲካ አመራሮች ለአገሪቱ መጠነ ሰፊ ችግሮች የብሔራዊ መግባባት ውይይት አለመደረጉን በምክንያትነት ሲጠቅሱ በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡


Read 933 times