Sunday, 23 August 2020 00:00

የአለም የጡት ማጥባት ሳምንት (August 1-7)

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

  ማንኛውም የእናቱን ጡት ወተት በተገቢው የጠባ  ህጻን የሕይወቱን ምእራፍ በተሟላ እና ምርጥ በሆነ ሁኔታ እንደጀመረው እርግጥ ነው፡፡
በአለም ላይ በየአመቱ ይሞቱ የነበሩ 820.000/ ህጻናት የእናት ጡት ወተት በመጥባት ምክንያት ከሞት እንዲተርፉ ምክንያት ሆኖአል፡፡
August 1-7 የአለም የጡት ማጥባት ሳምንት እንዲሆን በአለም ላይ በተለያዩ ሀገራት ትኩረት እንዲያገኝ በማሰብ የተወሰነ ነው፡፡ በእርግጥ አስቀድሞ የነበረው ቀን የአለም የጡት ማጥባት ቀን ሲሆን የሁዋላ ሁዋላ ግን እለቱ ወደሳምንት በማደግ የአለም የጡት ማጥባት ሳምንት በሚል የአንድ ሳምንት ጊዜ ተሰጥቶ ታል፡፡  ጡት ማጥባት ምንጊዜም ይቅር የማይባል ህጻናቱን በጤንነትና በደህንነት ለማሳደግ የእናቶችና የመላው ህብረተ ሰብ ኃላፊነት በመሆኑ ይህንን የሚያስ ገነዝብ ሳምንት እንዲሆን በተባበሩት መን ግስታት ስር ያሉ በርካታ ሀገራት ያመኑበትና የተስማሙበት ሳምንት ነው፡፡
የአለም የጡት ማጥባት ሳምንት መከበር የጀመረው እ.ኤ.አ በ1992 ዓ/ም ነው፡፡ ይህ እለት በተለያየ መንገድ በየሀገራቱ መከበር ከጀመረ ከተወሰኑ አመታት በሁዋላ በአለም የጤና ድርጅትና በአለም የህጻናት ድርጅት እንዲሁም በየሀገራቱ በሚገኙ መንግስታዊና  መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ የሚመለከታቸው አካላትና ግለ ሰቦች ጭምር በተሳተፉበት የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ 120/ አገራት አክብረው ታል፡፡  እለቱ እንዲሰየም የሆነውም በአለም ላይ ያለውን የጡት ማጥባት ልምድ ለማሳደግና ለማበረታታት እንዲሁም አስፈላጊ መሆኑን በጽኑ ለማሳየት እና የጡት ማጥባት ዋነኛ ግቦች ምን እንደሆኑ፤ በእናትና ልጅ መካከል መቼም ሊወገድ የማይችል ክቡር ተግባር መሆኑን ለመጠቆም እንዲያስ ችል ነው፡፡ ልጅን ጡት ማጥባት እናትየውንም ሆነ ልጁን በጤናማነት እንዲኖሩ የሚያደርግ ክቡር ተግባር ነው፡፡የጡት ማጥባት ሳምንት በየአመቱ የሚያሳስበው
እናቶች እንደወለዱ በመጀመሪያ የሚገኘውን እንገር የተሰኘ የጡት ወተት ለልጁ በመስጠት የልጁን ጤንነት በመጠበቅ በኩል ልክ እንደክትባት አስፈላጊ መሆኑን፤
ማንኛዋም እናት ልጅዋን ከወለደችበት ቀን ጀምሮ እስከስድስት ወር ድረስ ካለም ንም ድብልቅ የጡት ወተቷን ብቻ እንድትሰጥ፤
ከተቻለም ከስድስት ወር በሁዋላም ህጻኑ ሌላ ምግብ እየተመገበ በተጨማሪ እስከ ሁለት አመት ድረስ የእናት ጡት ወተት ማጥባቱን እንድታከናውን ይመክራል፡፡   
የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም እና የዩኒሴፍ ዳይሬክተር  Henrietta H. Fore 31 July 2020 በጋራ ባወጡት መግለጫ የ2020/ የአለም የጡት ማጥባት ሳምንት መሪ ቃል “Support breastfeeding for a healthier planet” የሚል ነው፡፡ የዚህ አባባል ስሜትም ጤናማ የሆነች አለምን እውን ለማድረግ ለጡት ማጥባት የተቻለውን ያህል ድጋፍ ማድረግ እንደ ሚገባ የሚያሳይ ነው፡፡ በዚህም መንግስታቱ ሁሉ እናቶች ልጆቻ ቸውን ጡት ማጥባት የሚያስችላቸውን እውቀት እንዲያገኙ የሚያስችላ ቸውን አቅም ማጎል በት የሚያስችል የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ዳይሬክተሮቹ አስገንዝዋል፡፡  
የእናት ጡት ወተትን ለህጻኑ ማጥባት ህጻኑ የህይወቱን እርምጃ በበጎ እና ምርጥ በሆነ አስተዳደግ መጀመሩን ያሳያል፡፡
የእናት ጡት ወተት ለህጻኑ መስጠት የልጁንም ሆነ የእናትየውን ጤንነት በመጠበቅ ህጻኑ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኝ ያስችለዋል፡፡
የጡትዋን ወተት እየመገበች ልጅዋን ያሳደገች እናት የሚጠበቅባትን ተግባር እንዳከናወነች በማሰብ ስሜትዋ በፍጹም አይጎዳም፡፡
በእርግጥ የእናት ጡት ወተትን ለተወለደ ልጅ ማጥባት ተፈጥሮአዊ ቢሆንም ሁልጊዜ ቀላል ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህም እናቶች ጡት ማጥባቱን ለመጀመርም ሆነ ሳያቋርጡ ለመቀጠል ድጋፍ ሊያገኙ ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህም አቅማቸውን ለማጎልበት የሚረዳ ሙያዊ የሆነ የምክር አገልግሎት ማግኘት አለባቸው፡፡ በእርግጥ በየአመቱ እየጨመረ በመምጣት ላይ ባለው የእናት ጡት ወተት ማጥባት ምክንያት በአለም ላይ በየአመቱ ይሞቱ የነበሩ 820.000/ ህጻናት ከሞት እንዲተርፉ ምክንያት ሆኖአል፡፡
እ.ኤ.አ በ2020 በተከበረው የአለም የጡት ማጥባት ሳምንት ጡት የሚያጠቡ እና ቶች ተመጣጣኝ የሆነ እና ጤናማ ምግብ መመገብ እንደሚገባቸው የጠቆሙ ሲሆን በአምስት የተከፈሉት የምግብ አይነቶቹም እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
ፎሊክ አሲድ፡- ቫይታሚን B9 በተባለው ንጥረ ነገር የበለጸገ ሲሆን ህጻኑን ልጅ አዲስና ጤናማ ሴል እንዲያገኝ እንዲሁም የአእምሮውን ጤንነት የተሟላ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ይህ ንጥረ ነገር ከባቄላ ፤ጥቁር አረንጓዴ ምግቦች… ወዘተ ከመሳሰሉት ምግቦች ይገኛል፡፡
በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦች፤ በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ የህጻኑን ደህንነትና እድገት የተስተካከለ እንዲሆን ለማድረግ እና ለዚህ የሚረዳውን የጡት ወተት ለማም ረት ያግዛል፡፡ የሚያጠቡ እናቶች ከምግባቸው በቀን 25/ግራም ፕሮቲን ማግኘት አለባቸው፡፡ የሚያጠቡ እናቶች በየቀኑ በቁርስ፤ በምሳ እና በእራት በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ አለባቸው፡፡ ጥሩ ፕሮቲን አላቸው ከሚባሉት ምግቦች መካከል ጥራጥሬዎች፤ ለውዝ፤ ከወተት ተዋጽኦ የሚገኙ፤ ዶሮ፤ ስጋ፤ አትክልት…  ወዘተ፤
በአይረን የበለጸጉ ምግቦች፤ በአይረን የበለጸጉ ምግቦች የሚፈለጉበት ምክንያት  የእናትየውንም ሆነ የልጁን የቀይ የደም ሴል የሚያበለጽግ እና የህጻኑ አእምሮ ለማደግ አይረንና ኦክስጂን ስለሚያስፈልገው ነው:: በተጨማሪም ድካምና አንዳድ የአቅም ማነስ ሁኔታዎች እንዳይከሰቱ ያገለግላል፡፡ የህጻኑ ሰውነትና አእምሮ ለማደግ አይረንና ኦክስጂን የተባሉትን ንጥረነገሮች ይፈልጋል:: ምግቦቹም እንደ ስጋ በተለይም ጉበትና ኩላሊት፤ አረንጉዋዴ ቅጠላ ቅጠሎች፤ የተቀቀለ ባቄላ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ አይረን ያለባቸውን ቅጠላ ቅጠሎች በሚወሰዱበት ጊዜ አይረኑ ከሰውነት እንዲዋሃድ በተመሳሳይ ቫይታሚን ሲን የያዙትን እንደ ቲማቲም ብሮኮሊ ወይንም ፍራፍሬን መጠቀም ይመከራል፡፡ እንደሻይ እና ቡና የመሳሰሉት መጠጦች የአይረንን ጠቀሜታ ስለሚገድቡት በተቻለ መጠን አወሳሰድ ላይ መቀነስ ይበጃል፡፡
በካልሲየም የበለጸጉ ምግቦች፤ በቀን እስከ 1000/ሚሊግራም ካልሲየም በየቀኑ ለምታጠባ እናት ያስፈልጋታል፡፡ ይህም ለወደፊት የአጥንት መሳሳት በእናትየው ላይ እንዳይከሰት ይረዳል፡፡ ምግቦቹም የወተት ውጤቶች፤አረንጉዋዴ ቅጠላ ቅጠሎች፤ ሶያ…ወዘተ ናቸው፡፡
በባህል የሚታመንባቸው የእናት ጡት ወተት እንዲፈጠር እና ጡት ምንጊዜም ሙሉ እንዲሆን ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ እንደ ገብስ፤ አጃ፤ ጎመን፤ የመሳሰሉትን ምግቦች መመገብ ጠቃሚ ነው፡፡

Read 8564 times