Tuesday, 25 August 2020 05:11

ከፌስቡክ ገጾች በጨረፍታ

Written by  (ስመኝ ግዛው)
Rate this item
(0 votes)

 “ሥራህን ሥራ! ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ተሰጥቶታል፤ ያንን መሥራት የእሱ ፈንታ ነው››
                         (ስመኝ ግዛው)


          ከላይ ርዕስ ያደረገኩት ኢንጂነር ታከለ ዑማ፤ ;የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ወጣቶች፣ የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ያበረከቱልኝ ልብ የሚነካ የፅሁፍ ስጦታ ነው; ብለው በፌስቡክ ገፃቸው ያሰፈሩትን ቃል ነበር፡፡ ለከተማችን - ለነዋሪዎቻችን ብዙ ሠርተዋል፤ የሚታይ ስራ ሰርተዋል፡፡ ለነዋሪዎች ቅርብ ነበሩ፡፡
በተማሪዎች ልብ፣ በብዙ ወላጆች መንፈስ ውስጥ ነበሩ፡፡ በተማሪዎች ምገባው፣ በዩኒፎርሙ፣ በት/ቤት አውቶብሱ፣ በቤት እደሳው፣ በምግብ ባንኩ፣ በአረንጓዴ አሻራው፣ በሸገር ዳቦው፣ በበጎ ፈቃድ ስራዎች፣ 8ሺ በላይ ተመራቂዎችን በስልጠና በመደገፍ ስራ በማስያዝ….በብዙ ብዙ ውጤታማ ስራዎች ይታወሳሉ፡፡ ወደ ሰው ሲቀርቡ የፈካ ፊትና ገፅታ፣ ትህትና የተሞላበት ሰውነት ይታይባቸዋል፡፡ ዘናጭም ናቸው፡፡ አለባበስ ያውቁበታል፡፡ ከባለስልጣንነታቸው በላይ ጓደኛዊ ቤተሰባዊ ስሜታቸው ይቀድማል፡፡
ሁላችንም ባለንበት የምንችለውን ካደረግን በቂ ነው! ማን ሙሉ ነውና?

Read 1134 times