Tuesday, 25 August 2020 06:21

“Super Goal Spoken English” መፅሀፍ ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በዮሃንስ ተስፋዬና ታረቀኝ ጥላሁን የተሰናዳውና እንግሊዝኛን አቀላጥፎ ለመናገር ያግዛል የተባው “Super Goal Spoken English” የተሰኘ መፅሀፍ ለገበያ ቀረበ።
መፅሃፉ እንደ ማጠቀሻና እንግሊዝኛን ለመናገር እንደ መለማመጃ ሆኖ እንደሚያግዝ የገለፁት አሰናጆቹ፣ በጀማሪነት፣ በመካከለኛ ደረጃና በከፍተኛ ደረጃ ላሉ እንግሊዝኛ ተለማማጆች እንዲመች ተደርጐ መሰናዳቱንም በመግቢያው አስፍረዋል።
ከ15 አመታት በላይ በእንግሊዝኛ መምህርነት የቆዩት የመፅሃፉ አዘጋጆች ሰዎች ሌሎች ቋንቋዎችን ለማወቅ የሚያስፈልገው ልምምድ መሆኑን በማመን ከሰዎች የዕለት ከእለት እንቅስቃሴ ጋር የሚገናኙ የተለያዩ ሃሳቦችንም እንዳካተቱ ገልፀዋል። በ193 ገፆች የተቀነበበው መፅሃፉ በ150 ብር ለገበያ ቀርቧል።
“እንስሳትን ያማከሉ እንቆቅልሾች” እና “እኔ ምንድን ነኝ” የተሰኙ መጽሐፍት ለንባብ በቁ
በገላውዲዮስ አለልኝ የተፃፉ “እንስሳትን ያማከሉ እንቆቅልሾች” እና “እኔ ምንድን ነኝ” የተሰኙ ሁለት የእንቆቅልሽ መጽሐፍት ለንባብ በቁ፡፡
ሁለቱም መጽሐፍት በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተፃፉና የእንቆቅልሽ አይነቶችና ሂደቶችን የሚተነትኑ ሲሆኑ፣ በተለይ ለልጆች ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውንና እውቀታቸውን ለመገንባት መጽሐፍቱ በእጅጉ ጠቀሜታ እንዳላቸው የመጽሐፍቱ አዘጋጅ ገልጿል፡፡
“እኔ ምንድን ነኝ” የተሰኘው መጽሐፍት በ116 ገጽ ተቀንብቦ በ60 ብር ለገበያ ሲቀርብ፣ “እንስሳትን ያማከሉ እንቆቅልሾች” የተሰኘው ደግሞ 114 ገፆች ተቀንብቦ በ60 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

Read 6797 times