Saturday, 21 July 2012 12:12

በደስታ የተሞሉ ትዳሮች ምስጢር...

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

በቅርቡ አንዲት ተሳታፊ የላከችልን ደብዳቤ እንዲህ ይላል፡፡ ..እኔ ከባለቤ ጋር በትዳር ስኖር ወደ አስራ ስድስት አመት ይሆነናል፡፡ ባለቤ እና እኔ በፍጹም ተግባብተን ወይንም ፍቅርን እርስ በእርስ ስንገላለጽ ታይተን አናውቅም፡፡ እሱ በበኩሉ እስዋ ለእኔ ሳይሆን ትኩረት የምትሰጠው ለቤ ተሰቦቿ ነው ይላል፡፡ እኔ ደግሞ በበኩሌ ምንጊዜም ፍቅሩን ገልጾልኝ እንደማ ያውቅ መመስከር ብቻ ሆነ ስራዬ፡፡ በሁዋላም አንዳንድ የማቀርባቸውን ሴቶች ማማከር ስጀምር ...አይ... ያንቺ ባለቤት አረ... ጥሩ ሰው ነው፡፡ የእከሊትን ብታይው ምን ልትይ ነበር...አረ የአቶ እከሌ ሚስት የተናገረችውን ብትሰሚ ...የሚል ትችት ተሰነዘረ፡፡ ወደሌሎቹ ጋ ደግሞ ስሄድ በጎ የሚባሉ ነገሮች በእኔ ቤት ካለው ኑሮ ምንም የተለየ ሳይሆን አገኘሁት፡፡ በሁዋላም ባለቤን እባክህን እንነጋገርና የምናስተካክላቸውን ነገሮች እናስተካክል ብዬ ብጋብዘው ሞቼ ነው... ወይንስ ቆሜ...ከዚህ በሁዋላ ከአንቺ ጋር ኑሮ የሚሉት ነገር አልሞክረውም ብሎ ቁጭ አለ፡፡

እርሱ ለካስ እስከጭርሱንም ለፍቺ ተዳርሶ ኖሮአል፡፡ ለማንኛውም እኔም ሀሳቤን እንደገና ወደ ጸብ መልሼ ለፍቺ እየተደራደርኩ ነው፡፡ ምክንያቱም አኔን ለመፍታት ካሰበ ከሌላ ሴት ጋር መውጣት ጀምሮአል የሚል ጥርጣሬ ስለገባኝ ነው፡፡ በእርግጥ ትዳሬን እወድ ...አከብር ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ከአቅሜ በላይ ስለሆነ ወደ ውሳኔ እያመራሁ ነው፡፡ አንድ ነገር መጠቆም የምፈልገው ነገር ግን አለ፡፡ ምናለ...በእኛም አገር በትዳር ጉዳይ ላይ ምክርን የሚሰጡ ተቋማት ቢኖሩ... በእርግጥ አሉ የሚባል መረጃ አለኝ፡፡ ነገር ግን በቀላሉ ሁሉ ሰው ሊያገኛቸው በሚችል መልክ ቢዋቀሩ ጥሩ ነው ባይ ነኝ፡

 

ሔለን አሰፋ/ከቦሌ/

ሔለን በሰጠችው ጥቆማ መሰረት ሁኔታዎቹን የሚመለከት መረጃን አግኝተናል፡፡ በእርግጥ በትዳር ጉዳይ ላይ የምክር አገልግሎት የሚሰጡ ቢኖሩም ሔለን እንዳለችው በቀላሉ ለሁሉም ሰው ምቹ በሆነ ሁኔታ ስለማይገኙ ወደፊት ይስፋፉና የተሸ አገልግት ይሰጣሉ የሚል እምነት አለን፡፡ ለጊዜው ግን በመጠኑም ቢሆን እገዛ ሊያደርጉ የሚችሉ ነጥቦችን ወደአማርኛ መልሰን እነሆ ለንባብ ብለናል፡፡ ለአመታት ዘልቀው ሞት እስኪለይ ድረስ በደስታ የሚሞሉ ትዳሮች ዋነኛውና ቁልፊ ሚስጥር መነጋገር ወይም ውይይት ማድረግ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገ ራሉ፡፡ ይህ ደግሞ የትዳር አጋርዎን ስሜት የማንበብ ብቃት እንዲኖርዎትና በተመሳሳይ ሁኔታ የትዳር አጋርዎም የእርስዎን ስሜት ለማንበብና ለመረዳት እየሞከራችሁ መሆኑ እንደሆነ ካመኑ ትዳርዎ በመደጋገፍና በመረዳዳት ስለሚሞላ መንፈሳዊ እርካንታን እንደ ሚሰጥ ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

ትዳርን በደስታ በመተማመንና በፍቅር የተሞላ እንዲሆን ከሚያደርጉ ምስጢሮች ውስጥ አንዱ ለትዳር አጋርዎ ስሜታዊ ጉዳት ርህራሄ ማሳየት ነው፡፡ ይህ ሆነ ማለት ደገሞ ስሜታዊ የሆነና መልእክቶችን መረዳት ሲችሉ በባህርይዎ ለትዳር አጋርዎ ስሜ ታዊ ጉዳት ርህራሄን ለማጎልትዎ ዋነኛው ምክንያት ይሆናል፡፡ እነዚህ መልእክቶች በቃ ላት የሚገልጹት የመልእክት አይነቶች ባይሆኑም የትዳር አጋርዎ ከእርሳቸው ጋር በቂ ጊዜ እያሳለፉ እንዳልሆነ የሚወቅስ መልእከት በቃላት ጽፈው ሊልኩልዎት ይችላሉ፡፡ ይሁ ንና ስሜታዊው መልእክት ከዚህ የተለየ በመሆኑ ምናልባትም ..ናፍቀሽኛል...ናፍ ቀኸኛል... ነገር ግን እኔ ላንተ/ላንቹ ያን ያህል አስፈላጊ የሆንኩ አይመስለኝም.. የሚል መልእክት ያዘለ ስሜትን ከትዳር አጋርዎ ላይ ካነበቡ...ለእኚህ ትዳር አጋርዎ ለተከፋው ስሜት ርህራሄንና ሀዘኔታን በማጎልበት ሁኔታውን ሊያስተካክሉ ይገባል፡፡

ትዳርን የተመቻቸና በደስታ እንዲሞላ ከሚያደርጉት ሚስጥሮች ውስጥ ሌላው ነጥብ ደግሞ የራስዎን ስሜታዊነት ገታ በማድረግ ትዳርዎ እንዳይበጠበጥ ማድረግ ነው፡፡ በመካከላችሁ በሚፈጠር አለመግባባት ምክንያት የትዳር አጋርዎ ስሜታዊነታቸው አይሎ በንዴትና በቁጣ ተሞልተው ሊያናግርዎት ይችላሉ፡፡ ለእንደዚህ ዓይነቶች ንግግ ሮች ደግሞ ተከላካይ የሆኑ አሊያም አጋርዎ የሚናገሩት ነገር ስህተት እንደሆነ እየነገሩ በክርክር መመላለሱ ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁንና ይህ የቃላት ልውውጥ ከፍተኛ አለ መግባባትን ሊፈጥር ስለሚችል የትዳር አጋርዎን እንደዚያ ሊያናግራቸው የቻለው ስሜት መነሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ሊመረምሩ ይገባል፡፡ ከበስተጀርባ ያለውን ስሜት መነሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ሊመረምሩ ይገባል ፡፡

ከፍተኛ አለመግባባትን ሊፈጥር ስለሚችል የትዳር አጋርዎን እንደዚያ ሊያናግራቸው የቻለው ስሜት መነሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ሊመረምሩ ይባል፡፡ ከበስተጀርባ ያለውን ስሜት ከተረዱ የትዳር አጋርዎ ጥያቄ ለምሳሌ ያህል ..ብዙውን ጊዜ አብረን እያሳለፍን አይደለም፡፡ ..የሚል ከሆነ ..ምን ለማለት ፈልገሽ/ፈልገህ ነው..ትናንትና እኮ አብረን የእግር መንገድ ሄደናል፡፡ ባለፈው ሳምንት ደግሞ ምግብ ቤት ሄደን እራት አብረን በልተናል.. ብሎ መሞገቱ ፋይዳ የለውም፡፡ ይልቁንስ የትዳር አጋርዎ እርስዎን እንደናፈቁና ረዘም ያለ ጊዜ ከእርሶ ጋር ማሳለፍ እንደፈለጉ ይሄንንም እርስዎ እንዲ ያውቁ የትዳር አጋርዎ ማስረዳታቸውን አመስግነው እንደሚያፈቅሯቸው በመንገር የተበሳጨውንና የተከፋውን የትዳር አጋርዎን ስሜት ሊያድሱ ይገባል፡፡

ለጥሩና ደስተኛ ትዳር መሰረት ከሚሆኑት እውነታዎች ውስጥ አንዱ ለትዳር አጋር ጥሩ/ቅን መሆንና ማንኛውም አይነት አለመግባባት ሲፈጠር የማንኛችሁም ስሜት ሳይጎዳ በተረጋጋ መንፈስ መነጋገር ወሳኝ ነው፡፡ ደስተኛ የሆኑ ጥንዶች እንዳቸው ለአን ዳቸው ጥሩ ከመሆናቸው የተነሳ በመካከላቸው ባለው የአብሮነት ቁርኝት ምክንያት አን ዳቸው አንዳቸውን ..ምን ላግዝ...ምን ልስራ.... ብለው ይጠይቃሉ፡፡ እንደነዚህ አይ ነቶቹ ጥንዶች አንዳቸው አንዳቸው ላይ መጥፎና አስቀያሚ የሆነ ድርጊት የማይፈ ጥሩ በመሆ ናቸው የፍቅር ትስስራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና እየጠነከረ ይመጣል፡፡

ለትዳር በጎነት ቅመም ከሆኑ ነጥቦች ውስጥ  የሚመከረው ሌላው እውነታ ደግሞ ከትዳር አጋርዎ ጋር ለመተኛት አልጋ ላይ ከወጡ በሁዋላ ወዲያው እንዳይተኙ ነው፡፡ ይህ የሚመከረው ደግሞ ከአጋርዎ ጋር ለተወሰኑ ደቂቃዎች ማውራት እንዲችሉ ነው፡፡ አልጋ ላይ ሆናችሁ ማውራታችሁ ቀን በየፊናችሁ ስትውሉ ያጋጠማችሁንና ውሎአችሁን እንድትረዱ ይረዳችሁዋል፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ለቀጣዩ ኑሮአችሁ እቅድ እንድታወጡና በተረጋጋ ስሜት በመመካከላችሁ ተፈጥረው ስለነበሩ ችግሮች እንድት ወያዩ ስሚረዳ ነው፡፡

ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ አስተዳደግና ባህርይ ስላለው ማንነት ከሰው ሰው ይለያያል፡፡ ይህ በመሆኑ ደግሞ በእርስዎና በትዳር አጋርዎ መካከል ልዩነቶች ሊኖሩ ግድ ስለሚሆን ልዩነቶቻችሁ ላይ መወያየቱ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ ሲሆን ጉዳዮቻችሁ ላይ በጠረጴዛ ዙሪያ በመወያየታችሁ ቂም አሊያም ቁርሾ የሚያያይዝ ስሜት ስለማይኖር ውይይቱ ግንኙነትዎች ደስተኛና ጥሩ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

በፍቅር መሀከል ውይይት መኖሩ ዘላቂ የሆነን ጥሩ ስሜትንና ደስተኝነትን በትዳር ላይ ይፈጥራል፡፡ ይሁንና አንዳንድ ጥንዶች ላይ እንደሚስተዋለው ውይይት በሚያደርጉበት ጊዜ እያንዳንዷን ነገር በዝርዝር የመወያየት ልምዳቸው ትዳራቸው ለመበጥበጡ መንስኤ ይሆናል፡፡ ደስተኛ የሆኑ ጥንዶች ሲወያዩ እያንዳንዱን ዝርዝር ጉዳይ ላይ አበጥሮና ጠልቆ መነጋገርን አይመርጡም፡፡ በመሆኑም እንዲህ አይነት ጥንዶች ስሜት ለስሜት ስለሚግባቡ የአንዳቸውንም ስሜት ሳይጎዱ ቀለል ያለ ውይይትን ያደርጋሉ፡፡ በመሆኑም ..ውሀ ቀጠነ.. አይነት ወሬን በውይይታቸው ውስጥ የማያካትቱ ጥንዶች ደስታቸው ሳይፈርስ ትዳራቸው መዝለቅ ይችላል፡፡ ይሁንና በትዳር ውስጥ አለመስማማቶች ላይፈጠሩ አይችሉም፡፡ ይሁንና ደስተኛ የሆኑ ጥንዶች አሊያም ትዳራቸውን የሚወዱ ሰዎች ..ጥቃቅን..ተብለው የሚፈረጁትን የግጭት አይነቶችን በማስወገድ ሁኔታው ወደ ከፍተኛ ጸብ ሳያመራ ሁኔታዎቹን ለስለስና ቀላል አድርገው የማለፍ ብቃታቸው ለሁሉም ጥንድ የሚመክር እንደሆነ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ፡፡

 

 

Read 5420 times Last modified on Saturday, 21 July 2012 12:17