Saturday, 12 September 2020 12:29

እስከ ጳጉሜ ከ6 መቶ ሺህ በላይ ዜጐች በጐርፍ ተጠቅተዋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 እስከ ጳጉሜ ባለው የክረምት ወቅት ከ6 መቶ ሺህ በላይ ዜጐች በጐርፍ መጠቃታቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ሪፖርት አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ በድረ ገፁ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ፤ በክረምቱ በአፋርና በኦሮሚያ የተጠበቀው የጐርፍ አደጋ መከሰቱን ጠቁሞ፤ በዚህም ከ6 መቶ ሺህ በላይ ዜጐች መጐዳታቸውንና ከ220ሺህ በላይ ደግሞ መፈናቀላቸውን አመልክቷል፡፡
በዋናነት የአዋሽ ወንዝ ሙላት በተፋሰሱ የታችኛው መዳረሻዎች በፈንታሌ ወረዳ፣ መተሃራ ከተማና በአፋር ከዚህ በፊት ከነበረው የላቀ መጥለቅለቅ ተከስቶ ሰዎችን ከማፈናቀሉ በተጨማሪ፤ ከ16ሺህ ሄክታር በላይ የእርሻ ሰብል ማውደሙ ታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ በ2012 ክረምት በአጠቃላይ ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጐች በጐርፍ እንደሚጠቁ ተንብዮ የነበረ ሲሆን እስካሁን ከትንበያው ሩብ ያህሉ መከሰቱን ተመልክቷል፡፡
የክረምቱ ሁኔታም ቀጣይነት ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ አሁንም የጐርፍ ስጋቱ እስከ መስከረም እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡

Read 4088 times