Saturday, 12 September 2020 13:31

የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ “እውነቱ ሲገለጥ” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

   በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ “እውነቱ ሲገለጥ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ሰሞኑን ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡ በ208 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ የፖለቲካ ሴራዎችና የሌሎች ያልተሠሙ ሚስጥሮችን ከእነትንታኔው የቀረበበት ነው ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ በስፋት የሚገለፁ ሃሰተኛ ትርክቶችና ታሪካዊ እውነቶች፣ በኦሮሚያ ያሉ ፖለቲካዊ ሴራዎች እንዲሁም የለውጡ ሃይሎችና ሌሎችም በመጽሐፍ በስፋት እንደተዳሰሱ ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም የባህርዳሩ የሰኔ 15 ቀን 2011 ምስቅልቅልና በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ እስከ ዛሬ ያልተሠሙ ሚስጥራዊ ድርድሮችን ያካተቱ አጀንዳዎችም በመጽሐፉ መዳሰሳቸው ታውቋል፡፡
ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከዚህ ቀደም “የነፃነት ድምፆች”፣ “ሞጋች እውነቶች”፣ “ኢትዮጵያዊነትን የመመለስ ተጋድሎ” እና “ከገባንበት መውጫ” የተሰኙ መጽሐፍትን ለአንባቢያን ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡

Read 25888 times