Friday, 25 September 2020 00:00

ጎግል የ3 ቢሊዮን ዶላር ክስ ተመሰረተበት

Written by 
Rate this item
(2 votes)

   ታዋቂው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጎግል በስሩ በሚያስተዳድረው ዩቲዩብ ድረገጽ አማካይነት የህጻናትን መረጃዎች ያላግባብ ጥቅም ላይ አውሏል በሚል በእንግሊዝ የ3 ቢሊዮን ዶላር ክስ እንደተመሰረተበት ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡
ኩባንያው ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ከ13 አመት በታች ዕድሜ ያላቸውን እንግሊዛውያን ህጻናት መረጃዎች ያለፈቃድ በዩቲዩብ አሰራጭቷል ተብሎ ክስ እንደቀረበበት የጠቆመው ዘገባው፤ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ካሳለፈበት 3.2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚከፍልና ገንዘቡ ለህጻናቱ በካሳ መልክ እንደሚከፋፈልም አመልክቷል፡፡

Read 10720 times