Saturday, 28 July 2012 10:08

...መሬት ጥሩ ማዳበሪያ ኖሮት...ዘሩ ይደርቃል፡፡..

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

...እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ተገላግያለሁ፡፡ ከሶስት ወር በፊት ግን የነበርኩበት ጭንቀት ከፍተኛ ነበር፡፡ ይኼውም እርግዝናዬ ወደሰባት ወር ከአስራ አምስት ቀን ገደማ ሲሆነው ሕይወት አልባ ሆኖ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ከሐኪሞቹ የተሰጠኝ ምክር ምጡ በራሱ ጊዜ እስኪመጣ መታገስ ኦለብሽ የሚል ነበር፡፡ ...አስቡት እስቲ...ይህ ነገር ለእኔ በጣም ከባድ ነበር፡፡ በቤት ውስጥም ከባለቤ ጋር ጸብ ሆነ፡፡ እሱ... ሐኪሞቹ እንዳሉት እኔን ሊያግባባ...ከጭንቀ ሊገላግል ሲሞክር...እኔ ደግሞ...አንተ ገንዘብ እንዳታወጣ ብለህ ነው፡፡...እኔ ብሞት ምን ቸገረህ... ማለን ቀጠልኩ፡፡ ምናለፋችሁ... ንግግሬ ከማንም ጋር ሊግባባ አልቻለም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እና ሆድ ታስብሰኛለች፡፡ ...በስብአብ ወወልድ...እንዴት ጽንሱ ሆድሽ ውስጥ ጠፍቶ...እስክትወልጂ ድረስ ጠብቂ ይባላል...እኔ ሰምቼም አላውቅ...ትለኛለች፡፡

በእንደዚህ ያለው ውጥንቅጥ ነገር ውስጥ እንዳለሁ...ያለውን ሁኔታ ባለቤ ለሐኪሙ አስረድቶ...በኦፕራሲዮን እንድወልድ ተደረገ፡፡ ...እዚህ ላይ እኔ መጠየቅ የምፈልገው አንድ ነገር ነው፡፡ ለመሆኑ ጽንስ በማህጸን ውስጥ እያለ ሲሞት ምጥ እስኪመጣ ጠብቁ መባሉ የተለመደ ነገር ነውን...ወይንስ ለእኔ የተሰጠ ውሳኔ ነው?..

ከላይ ያነበባችሁት ጥያቄ አለም ገብሩ የተባለች እናት የላከችልን ነበር፡፡ ይህ አጋጣሚ የአለም ብቻም ሳይሆን የሌሎችም እናቶች ስለሆነ ስለሁኔታው እንዲያስረዱን ዶ/ር መብራቱ ጀምበር የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስትን አነጋግረናል፡፡ ዶ/ር መብራቱ በአሁኑ ወቅት በብራስ የእናቶችና ሕጻናት ሆስፒታል በማገልገል ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡

ኢሶግ/ ጽንስ ሆድ ውስጥ ሕይወት ማጣት አለማጣቱን እናቶች ሊያውቁ የሚችሉበት ዘዴ ምንድነው?

ዶ/ር ጽንስ ሆድ ውስጥ መጥፋቱ የሚታወቀው እራሳቸው ታካሚዎቹ እድገቱ እንደሚያስቡት ሳይሆን ሲቀርና ለሐኪም ሁኔታውን ሲገልጹ ነው፡፡ እናቶች ልጄ እያደገ አይመስለኝም በሚሉበት ጊዜ እኛ ባለን የምር መራ ዘዴ ተጠቅመን ሁኔታውን እንከታተላለን፡፡ ይህንን አስተያየት የሚሰጡት ገና የጽ ንሱ እንቅስቃሴ በማይሰማበት ማለትም የእርግዝናው ጊዜ ገና አምስት ወር ሳይሞላው ነው፡፡ በተለይም የመጀመሪያ እርግዝና በሆነበት ወቅት እንቅስቃሴው ከአምስት ወር በፊት አይሰማም፡፡ ነገር ግን የሁለተኛው ጊዜ እርግዝና ከሆነ ከአራት ወር ተኩል ጀምሮ እንቅስቃሴው ሊሰማ ይችላል፡፡ በዚያን ጊዜ የሆዴ ከፍታ አልጨመረም...ወይንም ሰዎች ሆድሽ አላደገም ምን ሆነሽ ነው ይሉኛል...በመሳሰሉት መንገድ በሚገልጹበት ጊዜ ምርመራውን ይደረጋል፡፡

ኢሶግ/ የጽንሱን እንቅስቃሴ መቋረጥ አለመቋረጡን እናትየው ለምን ያህል ጊዜ በትእግስት መጠበቅ አለባት?

ዶ/ር/ በእድገት ላይ ያለ ጽንስ ይንቀሳቀሳል ሲባል የሚያርፍበት ሰአትም እንዳለው መዘንጋት የለበትም ፡፡ ይህ ማለት ግን ለቀናት ዝም ብሎ ይተኛል ማለት አይደለም፡፡ አንድ ጽንስ በእናቱ ሆድ ውስጥ እያለ በሰላሳ ደቂቃ ውስጥ ለአምስት ጊዜ ያህል ወይንም ከዚያ በላይ እንደሚንቀሳቀስ ሁሉም እናቶች ሊያውቁት ይገባል፡፡ በዚህ ረገድ ጥሩና ቀላል  የመቆጣ ጠሪያ ዘዴ የሚ ባለው ጠዋት ቁርስ ከበሉ በሁዋላ ለሰላሳ ደቂቃ ያህል ...ምሳ ከበሉም በሁዋላ ለሰላሳ ደቂቃ ያህል ...እራት ከበሉም በሁዋላ ለሰላሳ ደቂቃ ያህል ልብ ብለው ቢከታተሉ ሁኔታ ውን ሊረዱ ይችላሉ፡፡ ይህ ማለት ግን ጽንሱ ከምግብ ጋር በተያያዘ ብቻ ይንቀሳቀሳል ማለት ሳይሆን ለእናትየው ለመከታተል እንዲያመች ነው፡፡ የጽንሱ እንቅስቃሴ በሰላሳ ደቂቃ ውስጥ ከአምስት ጊዜ በታች ከሆነ በህይወት አለ ቢባልም እንኩዋን የጤንነቱ ሁኔታ ግን ሊያነጋግር ይች ላል፡፡ ስለ ዚህ እናቶች ሁኔታ ውን ለሐኪም በመግለጽ ወደከፋ ችግር ሳይሄድ ክትትል እንዲደረግለት ማድረግ ይጠበቅ ባቸዋል፡፡

ኢሶግ/ ጽንስ በማህጸን ውስጥ ሲሞት ለመውለድ ምጥ እስኪመጣ ቢጠበቅ ጥሩ ነው ሲባል ምን ማት ነው?

ዶ/ር ጽንስ በሆድ ውስጥ በየትኛውም የቆይታ ጊዜ ማለትም ገና ሲረገዝ ጀምሮ እስኪወለድ ድረስ ሊጠፋ ይችላል፡፡ነገር ግን ገና በሶስት ወር እድሜ ላይ ያለ ከሆነ በማንኛውም ጊዜ ማውጣት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም እስከ ሀያ ስምንት ሳምንት እንደውርጃ ስለሚቆጠር ነው፡፡ እርግዝናው ከሀያ ስምንት ሳምንት በላይ ከሆነ ግን ጽንሱ መጥፋቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ ለሶስት ሳምንት ያህል በመቆየት በምጥ እንዲወለድ ይመከራል፡፡ በእርግጥ ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እንዳለ መጥፋቱ ከተረጋገጠ በሁዋላ ለረጅም ጊዜ መቆ የት ስለ ሚከብድ ብዙ እናቶች ይውጣልን ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ይህም ከራሳ ቸው የመ ንፈስ ጭንቀት ከቤተሰብ ሁኔታ ጋር ከመሳሰሉት ይያያዛል፡፡ ሕክምናው የሚመክ ረው ግን የተፈጠረውን ነገር መመለስ ባይቻልም በቀጣይ የሚሰራውን ግን በጥሩ ሁኔታ ምንም ሕመም ሳያስከትል በተፈጥሮአዊ መንገድ ማገላገልን ነው፡፡ነገር ግን ምጡም ባይመጣ እንኩዋን በምጥ ማምጫ መድሀኒት ተሞክሮ እንድትገላገል የሚደረግ ሲሆን ይህም ካል ተቻለ ግን ወደኦፕራሲዮን መሄድ ግድ ነው፡፡ ነገር ግን ለማንኛዋም ወላድ ተፈጥሮአ ዊው መንገድ በትእግስት ተጠብቆ አልሆን ካላለ በስተቀር በኦፕራሲዮን መውለድ አይመ ከርም፡፡ ምጥ እስኪመጣ ድረስ ይጠበቅ ሲባልም የእናትየዋን ጤና ከምን ደረጃ እንዳለ በየአምስት ቀኑ ወይንም በየሳምንቱ ክትትል በማድረግና በመቆጣጠር እንጂ ለሁሉም እናቶች በተመሳሳይ ሁኔታ የሚተገበርም አይደለም፡፡ የቆይታ ጊዜው ከሶስት እስከ አራት ሳምንት ድረስ ነው ... ሲባልም ከዚያ በላይ ለማቆየት የማይቻልበት ጽንሱ በማህጸን ውስጥ ከጠፋ የእናትየው ሰውነት ችግሩን ለማጥፋት ሲል የሚፈጥረው ችግር ስላለ ነው፡፡ ይህም የእንግዴ ልጅ ኬሚካሎች በደምስሮች ይገቡና የደምን መጉዋጎል ያስከ ትላል፡፡ የዚህ ውጤት ደግሞ የእናትየውን የመዳን ኃይል ይቀንሳል፡፡

ኢሶግ/ ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እንዳለ መሞቱን እና ለመውለድ ምጥን መጠበቅ እንዳለባት ለእናትየው የሚነገረው በምን መንገድ ነው?

ዶ/ር ለእናትየውም ሆነ በቅርብ ላለ ቤተሰብ ስለሁኔታው በእርጋት ነው የምናስረዳው ፡፡ ይኼውም ሊከተል የሚችለውን የበለጠ ጉዳት ለመቀነስ ሲባል የሚወሰድ የህክምና ዘዴ መሆኑን በማስረዳት ነው፡፡ በእርግጥ ጽንሱ ከጠፋ በሁዋላ ይዘሽው ቆይ የሚለው ነገር በተለይም ለእናትየው እጅግ የሚከብድና የሚረብሽ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ቢሆንም ግን የተፈጠረውን ነገር ማሻሻል ስለማይቻል ትንሽ ቀናትን ታግሶ እናትየው ከኦፕራሲዮን ውጭ ያለምንም የጤና ጉዳት እንድትወልድ ማድረግ ይመረጣል፡፡ እናትየው መረበሽዋን አስወግዳ በቀጣይ ጤናማ ሆነ ሌላ ልጅ እንድትወልድ የሚያስችላትን መንገድ በጽሞና ነግረን እንድትቀበለው ማድረግ ተመራጭነት ያለው መንገድ ስለሆነ ብዙዎችን በዚህ መልክ አሳምነን ወደተፈለገው ጊዜ እናደርሳለን፡፡ ይህንን ለማስፈጸም የምንጠቀምባቸው ብዙ የምክር አገልግሎት ዘዴዎች ስላሉ በተግባር በማዋል እናትየውን በቀጣይ ጤናማ ሕይወት እንዲኖራት ለማድረግ ይቻላል፡፡

ኢሶግ/ ጽንስ በሆድ ውስጥ እንዳይጠፋ እናትየው ምን ማድረግ አለባት?

ዶ/ር ይህ በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡ ብዙዎች ልምዳቸውን ሲናገሩ በእርግዝና ጊዜ ክትትሉ ከሶስት ወይንም ከአራት ወር በፊት መጀመር የለበትም ሲሉ ይሰማሉ፡፡ ይህ ግን በፍጹም ስህተት ነው፡፡ አንዲት ሴት የወር አበባዋ መምጣት ከሚገባው ጊዜ ከተቋረጠ ምክንያቱ ምንድነው ስትል ወደሐኪም መሔድ አለባት፡፡ ምናልባትም የወር አበባዋ የቀረው በእርግዝና ወይንም በሌላ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ይህ የሚለየው ደግሞ  በሕክ ምና ምርመራ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የእናትየው የጤንነት ሁኔታ እርግዝ ናውን ተሸክሞ መቀጠል ይችላል አይችልም የሚለውም አስቀድሞውኑ ለመለየት የሚቻለው ወደሐኪም ሲቀርቡ ነው፡፡ እርግዝናው በጤናማነት እንዳይቀጥል የሚያደርገው ምንድ ነው... በሚል ሁኔታውን ፈትሾ ሕክምና በማድረግ በጤናማ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማድረግ የሚቻለው እናቶች ሐኪማቸውን ሲያማክሩ ነው፡፡ እንዲያውም አንዲት ሴት ገና ከማር ገዝዋ በፊት ወደሕክምና ባለሙያ ቀርባ ስለጤንነትዋ ያሉትን ሁኔታዎች መከታተል ይጠበቅባታል፡፡፡፡ ጽንስ በማህጸን ውስጥ እንዳለ ሊጠፋ የሚችለው በሁለት መንገድ ነው፡፡ አንደኛው ከጽንሱ ጋር በተያያዘ ምክንያት ሲሆን ሌላው ደግሞ ከእናትየው ጤን ነት ጋር በተያያዘ ነው፡፡ አንድ መሬት ጥሩ ማዳበሪያ ኖሮት ዘር ተዘ ርቶ ጥሩ ፍሬ ሊሰጥ የማያስችል ከሆነ ዘሩ ይደርቃል፡፡ የሰውም ሁኔታ ልክ እንደዚያው ነው፡፡ እና ትየው ጤነኛ ሆና እርግዝናው በጤንነት እንዲቀጥል ካልተቻለ ጽንሱ ሊቀ ጥል ስለማይ ችል ይቋረጣል፡፡ በጽ ንሱ ምክንያት ሲሆን ደግሞ የክሮሞዞም ትክክል አለ መሆን ...በሚያስ ከትለው ችግር ጽንሱ በውርጃ መልክ ወይንም የተወሰነ ጊዜ ቆይቶ እድገቱ እንዳይቀጥል የሚሆንበት አጋጣሚ አለ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የእንግዴ ልጁ በማህጸን ግድግዳ ላይ አድጎ በትክክል ጽንሱን ለመመገብና ለማሳደግ ካልቻለ ችግር ሊፈጠር ይችላል፡፡ እንደ ዚህ ያሉ ሰፊ ምክንያቶች ሊገለጹ የሚችሉ ሲሆን እንደገናም ምክንያቱ ምንም ሳይታወቅ ሊሞት የሚችልበት ሁኔታም አለ፡፡ ባጠቃላይ ግን ጽንስ በማህጸን ውስጥ እያለ መሞቱን ለማቆም እናቶች ያላሰለሰ የህክምና ክትትል ሊያደርጉ ይገባል፡፡

በስተመጨረሻ ለእናቶች ማስተላለፍ የምፈልገው መልእክት...

..አንዲት ሴት እንደ ስኩዋር...የደም ግፊት...ኤችአይቪ የመሳሰሉት ሕመሞች ቢኖሩባት አስቀድማ ከማርገዝዋ በፊት ሐኪምዋን ብታማክር በጥሩ ሁኔታ የእርግዝናዋን ጊዜ ጨርሳ በጤነኛ ሁኔታ ጤነኛ ልጅ ልትወልድ ትችላለች ፡፡ በአጠቃላይም የህክምና ክትትል ማድረግ ካረገዙ በሁዋላ ሳይሆን ከማርገዝ በፊትም መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ..

ዶ/ር መብራቱ ጀምበር የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት

 

 

 

Read 3280 times Last modified on Saturday, 28 July 2012 10:14