Print this page
Thursday, 01 October 2020 11:51

“ዲስፓሲቶ” በዩቲዩብ 7 ቢ. ጊዜ በመታየት 1ኛ ደረጃን ይዟል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ፖርቶሪኳዊው ድምጻዊ ሉዊስ ፎንሲ ያቀነቀነውና ዳዲ ያንኪ በአጃቢነት የተሳተፈበት “ዲስፓሲቶ” የተሰኘ ተወዳጅ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ በዩቲዩብ ድረገጽ 7 ቢሊዮን ጊዜ በመታየት በአንደኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
ዩቲዩብ ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ ሃፒ ድረገጽ እንዳስነበበው 5 ቢሊዮን ጊዜ ያህል በዩቲዩብ ተመልካቾች የታየው የኤድ ሼራን ተወዳጅ ሙዚቃ “ሼፕ ኦፍ ዩ” በሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ የዊዝ ካሊፋ “ሲ ዩ አጌን” 4.7 ቢሊዮን ጊዜ በመታየት ሶስተኛ ደረጃን ይዟል፡፡
የማርክ ሮንሰን “አፕታውን ፋንክ” በ3.9 ቢሊዮን፣ የፒኤስዋይ “ጋንጋም ስታይል”፣ በ3.8 ቢሊዮን፣ የጀስቲን ቢበር “ሶሪ” በ3.3 ቢሊዮን፣ የማሮን ፋይቭ “ሹገር” በ3.3 ቢሊዮን፣ የኬቲ ፔሪ “ሮር” በ3.2 ቢሊዮን፣ የኤድ ሼራን “ቲንኪንግ አውት ላውድ” በ3.1 ቢሊዮን እንዲሁም የዋን ሪፐብሊክ “ካውንቲንግ ስታርስ” በ3 ቢሊዮን እይታዎች እንደ ቅደም ተከተላቸው እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ የያዙ የዩቲዩብ የሙዚቃ ቪዲዮዎች መሆናቸውንም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡



Read 1121 times
Administrator

Latest from Administrator