Thursday, 01 October 2020 11:52

አነጋጋሪው መጽሐፍ በሳምንት ከ600 ሺህ ቅጅ በላይ ተሸጧል

Written by 
Rate this item
(0 votes)


           በአሜሪካዊው ደራሲ ቦብ ውድዋርድ የተጻፈውና ከአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የተደረጉ 18 ቃለመጠይቆችን ያካተተው “ሬጅ” የተሰኘ አነጋጋሪ መጽሐፍ ለህትመት በበቃ በመጀመሪያው ሳምንት ብቻ ከ600 ሺህ ቅጂ በላይ መሸጡን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ብዙዎች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረውና ከሳምንት በፊት ለአንባብያን የደረሰው መጽሐፉ፣ ለህተመት በበቃ በቀናት ጊዜ ውስጥ በአማዞን ድረገጽና በሌሎች ምርጥ ሽያጭ ያስመዘገቡ መጽሐፍት ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጡንና የወረቀት፣ የድምጽ፣ እና የኢሊክትሮኒክ ኪፒዎችን ጨምሮ በድምሩ 600 ሺህ በላይ ቅጂዎች እንደተሸጠ ዘገባው አመልክቷል፡፡ አሳታሚው ድርጅት ሲሞን ኤንድ ሹስተር ባለፈው ረቡዕ በሰጠው መግለጫ፣ መጽሐፉን ለአራተኛ ጊዜ በድጋሜ ለማተም ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝና ህትመቱ ሲያልቅ በወረቀት ታትመው ለገበያ የቀረቡ የመጽሐፉ ቅጂዎች ብዛት 1.3 ሚሊዮን እንደሚደርስም አስታውቋል፡፡
ደራሲው ከሁለት አመታት በፊት ለንባብ ያበቁትና በፕሬዚዳንት ትራምፕ ላይ የሚያጠነጠነው “ፊር” የተሰኘ መጽሐፍ በታተመ በመጀመሪያው ሳምንት ከ1 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች እንደተሸጡለት ያስታወሰው ዘገባው፣ እስካሁን ድረስ 2 ሚሊዮን ያህል ቅጂዎች መሸጣቸውንም አክሎ ገልጧል፡፡Read 2719 times