Thursday, 01 October 2020 12:37

"አዎንታዊነት" መጽሐፍ እየተሸጠ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   "የብርሃን ዘመን” የግጥም መድብል ለገበያ ቀረበ

          በአለማየሁ ንጋቱ ከበደ (ኢንጅነር) የተጸፈው “አዎንታዊነት” የተሰኘ መጽሐፍ ሰሞኑን ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡ መጸሐፉ  የተለያዩ የእውቀት ዘርፎችን የሚዳስስ፣ አዎንታዊ አስተሳሰብን የሚያዳብር እንዲሁም የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካና የኢትዮጰያዊነት እሳቤንም በስፋት የሚቃኝ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
የመጽሐፉ አዘጋጅ አለማየሁ ንጋቱ፤ ኢንጅነርና ኢኮኖሚስት ሲሆኑ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎችም ከመጀመርያ እስከ ሁለተኛ ድግሪ ተመርቀዋል፡፡ “አዎንታዊነት’’ በ292 ገጾች ተቀንብቦ፣ በ250 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
በሌላ በኩል፤ በደራሲና ጋዜጠኛ ብርሃኑ ደጀኔ የተጻፈ የግጥም ስብስቦችን የያዘው ;የብርሃን ዘመን” የግጥም መድበል ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡ 140 ግጥሞችን ያካተተው መድብሉ፤ በ163 ብር ነው ለገበያ የቀረበው፡፡

Read 3898 times