Print this page
Saturday, 03 October 2020 12:49

በአለማችን የመጀመሪያው የጠፈር የፎቶ ኤግዚቢሽን ተጀምሯል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

   በአለማችን ታሪክ በአይነቱ የመጀመሪያው እንደሆነ የተነገረለት የጠፈር የፎቶ ኢግዚቢሽን፣ ከመሬት በ130 ሺህ ጫማ ርቀት ላይ በሚገኝ የጠፈር አካባቢ ውስጥ መጀመሩን ብሪትሽ ጆርናል ኦፍ ፎቶግራፊ ከሰሞኑ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡
የአለማችንን ማህበረሰቦች የተለያዩ የህይወት ገጽታዎች የሚያስቃኙና በዋናነት “ግለኝነት፣ ማህበረሰብ፣ አንድነት” በሚል መርህ ላይ ያተኮሩ 400 ያህል የተለያዩ ፎቶግራፎች የተካተቱበት ይህ ኢግዚቢሽን፣ "1854 ሚዲያ" በተባለው ተቋም አማካይነት ከጠፈር ላይ ተቀርጾ በቅርቡ በፊልም ለተመልካቾች እንደሚቀርብ ተነግሯል።
45 ደቂቃ እርዝማኔ እንዳለው የተነገረለት የኤግዚቢሽኑ ሙሉ ፊልም በመጪወ ማክሰኞ ተሲያት ላይ በድረገጽ አማካይነት በቀጥታ ለተመልካቾች እንደሚተላለፍ የጠቆመው መረጃው፣ በኢግዚቢሽኑ ለእይታ የበቁት 400 ፎቶግራፎች የተመረጡት ፖርትሬት ኦፍ ሂዩማኒቲ ለተሰኘው አለማቀፍ የፎቶግራፍ ውድድር ከግለሰቦችና ከተቋማት ከተላኩት ፎቶግራፎች ውስጥ እንደሆኑም አክሎ ገልጧል።


Read 7454 times
Administrator

Latest from Administrator