Saturday, 03 October 2020 12:56

“ሰባተኛው ንጉስ” የአሮጊቷ ጠንቋይ ትንቢቶች መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ ተስፋዬ አየለ የተሰናዳውና አጫጭር ልቦለድ ታሪኮችን ያካተተው “ሰባተኛው ንጉስ” የአሮጊቷ ጠንቋይ ትንቢቶች በሚል ዋናና ንዑስ ርዕስ የተሰየመው መጽሐፍ ለንባብ በቃ መጽሐፉ በርካታ በማህበራዊ፣  በፖለቲካዊና በተለያዩ ሁነቶቻችን ዙሪያ የሚያጠነጥኑ አጫጭር ልቦለዶችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች በ18 ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ212 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ በ101 ብር ከ40 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡
ደራሲው ከዚህ ቀደም “የንጋት ሹክሹክታ” የግጥም መድብል፣ “ሽንቁርና ውታፍ” የተሰኘ የከድር ሰተቴ ታሪክ የተካተተበት አጫጭር ታሪኮች ስብስብ፣ “ODAA JALA” የኦሮሚኛ አጫጭር ልቦለድ ስብስብ ከሌላ ፀሐፊ ጋር እንዲሁም “መንገደኛው ባለቅኔ” የተሰኘ የከድር ሰተቴ ታሪክ ታሪካዊ ልቦለድ መጽሐፍትን ለንባብ አብቅቷል፡፡

Read 3432 times