Print this page
Saturday, 03 October 2020 13:04

የቢኒያም ወርቁ “ሕያው ብራና” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ከልቦለድ መጽሐፍ “ዳንሶስ” የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ ከቴአትር “ማን ለማን”፣ “የአልማዝ ቀለበት”፣ “ዱር ያደረ ፍቅር” እና “ሜዳሊያ” በተሰኙ ቴአትሮቹ ድርሰትና ዝግጅት ብሎም በትወና የምናውቀው ከያኒ ቢኒያም ወርቁ ሥራ የሆነው “ሕያው ብራና” የተሰኘ ልቦለድ መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ ከያኒው በመጽሐፉ በአገራችን በርካታ ያልተዳሰሱ ማህበራዊ ጉዳዮችን አንስቶ እኛነታችንን በቅጡ እንድንፈትሽና ሀብትና ቅርሶቻችንን እንድናውቅ የሚያሳስብበት መጽሐፍ ነው ተብሏል፡፡ መቼቱን በኢትዮጵያና በተለያዩ የዓለም አገራት የደረገ ሲሆን በርካታ አስገራሚ ጉዳዮችንና ገጠመኞችንም አካትቷል ተብሏል፡፡
በ206 ገጽ የተቀነበበው “ሕያው ብራና” በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ከያኒ ቢኒያም ወርቁ ከቴአትር ድርሰት ዝግጅትና ትወና በተጨማሪ በፊልም ድርሰትና ዝግጅትም ጉልህ አበርክቶ ያለው ሲሆን “አዲስ ሙሽራ”፣ “ሰባተኛው ሰው”፣ “የትሮይ ፈረስ”፣ “ቫኬሽን ፎርም አሜሪካ”፣ “በራሪ ልቦች” እና “ ወደ ገደለው” የተሰኙ ፊልሞችን ለእይታ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

Read 3336 times