Monday, 05 October 2020 00:00

“በእምነት ስም የተደራጁ ማፍያዎች” መጽሐፍ ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   የእውቁ ጋዜጠኛና ደራሲ ወርቅአፈራሁ 10ኛ ሥራ የሆነው “በእምነት ስም የተደራጁ ማፍያዎች” መጽሐፍ ለገበያ ቀረበ፡፡ መጽሐፉ በዋናነነት ፓስተር ነን፡፡ ከህመም እንፈውሳለን፣ ሰውን በሀብት እንባርካለን በማለት በእምነት ስም ተደራጅተው ማህበረሰቡን በማታለል ስለሚያደርሱት ግፍና በደል በስፋትና በጥልቀት የሚተነትነውም ተብሏል፡፡
አብዛኛው የመጽሐፉ ክፍል የነዚሁ ማፍያዎች ሴራ በየኔታ ቲዩብ ለተመልካች የተጋለጠበት ሲሆን ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ በመጽሐፍ መልክ ተሰንዶ ትውልድ እንዲማርበት መታተሙን ደራሲና ጋዜጠኛ ወርቀአፈራሁ አሰፋ ተናግሯል፡፡ የደራሲው 10ኛ ሥራ የሆነው ይሄው መጽሐፍ “በእምነትና ሥም የተደራጁ ማፍያዎች”፣ “ፖለቲካና ሀገር” እና “መንገደኛው ጋዜጠኛ” በሚሉ 3 ዋና ዋና ክፍሎች ተከፍሎ የተሰናዳ ሲሆን፤ በ220 ገጽ ተቀንብቦ በ180 ብር እና በ40 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 8978 times