Monday, 05 October 2020 00:00

“ሁለቱ ጊዮርጊሶች” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ እስማኤል ኃይለማርያም (መናኙ) የተፃፈውና በአንድ ጀምበር ከመገናኛ ፒያሳ የደርሶ መልስ ጉዞ በርካታ ነገሮችን ያሰፈረበት ሁኔታ የቃኘበት “ሁለቱ ጊዮርጊሶች” መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ በአንድ ጀምበር የ200 ዓመታት ታሪካችንን፣ በአንድ መንገድ ቀጥታ ታሪካችንን ቅርሶቻችንን የህይወት አጋጣሚዎቻችንን እያስቃኘ ከምንም በላይ ግን አትኩሮቱ አስተውሎቶቹንና ፍልስፍናዎቹን ከማህበራዊ ሂስ ጋር አዋህዶ በተዋጣለት የስነ - ጽሑፍ ለዛ የሚተርክበት ነው ተብሏል፡፡
ደራሲው በመግቢያው አንድ ሰው እያንዳንዱን እርምጃውን በአስተውሎትና በትኩረት ከተራመደ በርካታ አስገራሚ፣ ድንቅ አጋጣሚና አስተማሪ ነገሮችን ማግኘት እንደሚችል ገልፆ ሶስተኛ ሥራው የሆነው “ሁለቱ ጊዮርጊሶች” መጽሐፍም የዚህ ትኩረትና አስተውሎት ውጤት ስለመሆኑም አስታውሷል፡፡ በ12 ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ184 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፍ በ150 ብርና በ30 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም “አፍቃሪው መናኝ” እና “የስደተኛዋ ድምጽ” የተሰኙ መጽሐፎችን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡


Read 9233 times