Monday, 05 October 2020 00:00

“የአዕምሮ ህመሞችና ህክምናቸው” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በዶ/ር አብርሃም ክብረት የተዘጋጀውና በዘርፈ ብዙ መንስኤዎች ስለሚከሰቱ የአዕምሮ ህመሞችና ህክምናቸው ላይ ትኩረት አድርጐ የተሰናዳው “የአዕምሮ ህመሞችና ህክምናቸው” የተሰኘው መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ በስኪዞፍሬኒያና በሌሎች የሳይኮሲስ ህመሞች፣ በደስተኛነት መዛባት፣ በጭንቀት ወለድ፣ በማንነትን የመርሳት፣ በአልኮል መጠጥና ተያያዥ ጉዳዮች፣ በሱስና በተያያዥ ችግሮች፣ በወሲብ ችግርና በተያያዥ ህመሞች እንዲሁም በወንዶችና በሴቶች የአዕምሮ ህመሞችና ህክምናቸው ዙሪያ እንዲሁም በአዕምሮ ዝግመትና በርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ከነመፍትሔው ያመላክታል ተብሏል፡፡ በተጠኑ ጥናቶች በሀገራችን ከ100 ሰዎች 15ቱ የአዕምሮ ህመም እንደሚያጋጥማቸው የተገለፀበት ይህ መጽሐፍ ሁሉንም የአዕምሮ ህመሞች ከመዳሰሱም በተጨማሪ 110 የተለያዩ የአዕምሮ ህመሞችንና ህክምናቸውንም ያካተተ ሲሆን በ305 ገጽ ተቀንብቦ በ150 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ዶ/ር አብርሃም ክብረት ከዚህ ቀደም በስኳር ህመምና በእርግዝና ላይ ያተኮሩ ሁለት መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡


Read 37229 times