Saturday, 03 October 2020 00:00

ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ 50 ሚ. መራጮች ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል

Written by  መታሰቢያ ካሣዬ
Rate this item
(0 votes)

 ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ 50 ሚሊዮን መራጮች ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅና ለምርጫ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ ቦርዱ ትናንት ምርጫን አስመልክቶ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት ለጋዜጠኞች አስቃኝቷል፡፡
ለመራጮች ምዝገባ የተዘጋጁ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ያስጐበኘው ቦርዱ ለ50ሺ 900 የምርጫ ጣቢያዎች የሚሆኑ መዝገቦች መዘጋጀታቸውን አመልክቷል፡፡
የመራጮችን ድምጽ በግልጽ የሚያሳዩ 207ሺ የድምጽ መስጫ ሳጥኖች ተዘጋጅተዋል ያለው ቦርዱ፤ አንድ ጣቢያ አራት ድምጽ መስጫ ይኖረዋል ብሏል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት በጋዜጠኞች ከታዩት የምርጫ ቁሳቁሶች መካከል በአምስት ቋንቋዎች የተዘጋጁ የመራጮች መዝገቦች፣ የደህንነት መጠበቂያ ያለው የተመዘገቡ የመራጮች ካርድ፣ ለአስፈፃሚዎች የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች የሚገኙበት ሳጥን፣ የደህንነት መጠበቂያ ቁልፎች፣ በግልጽ የሚያሳዩ የድምጽ መስጫ ሳጥኖች፣ የምስጢር ድምጽ መስጫ መከላከያዎችና ሌሎችም በርካታ ቁሳቁሶች ይገኙበታል፡፡
ቦርዱ ለምርጫ ዝግጅት ካደረገባቸው ጉዳዮች መካከል ለመራጮች ምዝገባ የሚያከናውኑ 152ሺ 700 አስፈፃሚዎችና ለድምጽ መስጫ ቀን ደግሞ 254ሺ 500 አስፈፃሚዎች ዝግጁ መደረጋቸው ይገኙበታል ተብሏል፡፡   


Read 2826 times