Saturday, 28 July 2012 11:45

የእኛ ፍላጎት በኬሚካል ኢንዱስትሪው ጐልቶ መውጣትና መታወቅ ነው ቤካስ ኬሚካልስ

Written by  መንግስቱ አበበ
Rate this item
(0 votes)

ሐበሻ ሲሚንቶ ለደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች የ21 ሚሊዮን ዶላር አክሲዮኖች ሸጠ

በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኘው ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ የካበተ ልምድና ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ካላቸው ሁለት የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች ጋር በጋራ ለመሥራት ተፈራርሟል፡፡ የአክሲዮን ማኅበሩን አዋጪነት ተገንዝቦ 12 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ 27 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት የሆነው ፕሪቶሪያ ፖርትላንድ ሲሚንቶ (ፒፒሲ) ሲሆን የፋይናንስ ተቋሙ  ኢንዱስትሪያል ዴቬሎፕመንት ኮርፖሬሽን (አይዲሲ) ደግሞ በ9 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት 20 በመቶ ድርሻ በመያዝ አባል መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በደቡባዊ አፍሪካ ግንባር ቀደም ሲሚንቶ አምራች የሆነው ፒፒሲ፤ በደቡብ አፍሪካ፣ በቦትስዋናና በዚምባብዌ ስምንት የሲሚንቶ ፋብሪካዎችና ሦስት የመፍጫ ተቋሞች እንደሚያስተዳድር ታውቋል፡፡ በዓመት ስምንት ሚሊዮን ቶንስ (80ሚ. ኩንታል) ሲሚንቶ የሚያመርተው ፒፒሲ፤ በኢትዮጵያ ያደረገው ኢንቨስትመንት በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው መሆኑ ተገልጿል፡፡

እስካሁን ድረስ ከአገር ውስጥ ባለሀብቶች 400 ሚሊዮን ያህል ብር መሰብሰባቸውን የጠቀሱት የሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ የቦርድ ዳይሬክተር ኢ/ር ግዛው ተ/ማርያም፤ በዘርፉ ልምድ ካለው የውጭ ኢንቨስተር ጋር ለመሥራት ባደረጉት ጥረት፤ የደቡብ አፍሪካዎቹ ፒፒሲና አይዲሲ ኩባንያዎች ስለ አክሲዮን ማኅበሩ አንድ ዓመት ተኩል በጥልቀት ሲያጠኑና ሲደራደሩ ቆይተው፣ በ21 ሚሊዮን ዶላር የማኅበሩን 47 በመቶ ድርሻ መግዛታቸውን ተናግረዋል፡፡

ፒፒሲና አይዲሲ የሐበሻ ሲሚንቶን የፕሮጀክት አስተዳደርና ብቁ አመራር በጥልቀት አጥንተውና መርምረው፣ በአዋጪነቱ ተማምነው ኢንቨስት በማድረጋቸው ደስተኞች መሆናቸውን የጠቀሱት የኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢ/ር መስፍን አቢ፤ ሐበሻ ሲሚንቶ  በኢትዮጵያ ከፍተኛውን የኮንስትራክሽን ግብአቶች በማቅረብ ዓላማውን እንደሚያሳካ እርግጠኛ ነኝ ብለዋል፡፡

በመጀመሪያው ምዕራፍ በ130ሚ. ዶላር ሆለታ አካባቢ የሚሠራውና በ2006 ዓ.ም ይጠናቀቃል የተባለው ሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ፤ በዓመት 1.4 ሚሊዮን ቶንስ ሲሚንቶ በማምረት ወደ ገበያ እንደሚገባና በአጭር ጊዜ አቅሙን በእጥፍ በማሳደግ በዓመት 2.8 ሚሊዮን ቶንስ ሲሚንቶ ለማምረት መታቀዱን የኩባንያው ቦርድ ገልጿል፡፡

ኩባንያው ከባለአክሲዮኖች፣ ከፒፒሲና ከአይዲሲ ካሰባሰበው ካፒታል በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ86 ሚሊዮን ዶላር ብድር ማግኘቱን የጠቀሱት አመራሮቹ፤ በፋብሪካው ግንባታ ወቅት መቶ ዓመት ልምድ ያለው ፒፒሲ፤ የአመራርና የቴክኒክ ባለሙያዎችን ከማቅረቡም በላይ ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው አካዳሚው ሥልጠና ለመስጠት ማረጋገጫ መስጠቱን ተናግረዋል፡፡

ከ16ሺህ በላይ ባለአክሲዮናች ያሉት ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ፤ የተለያዩ የሲሚንቶ ዓይነቶችን፣ የተዘጋጀ አርማታ፣ የግንባታ ጠጠርና የጅፕሰም ምርቶችን ለገበያ እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡

 

 

Read 2991 times Last modified on Saturday, 28 July 2012 11:47