Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 28 July 2012 12:17

የላሊበላ ነዋሪዎች ሊነሱ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ለአካባቢውና ለቅርሱ ደህንነት፤ ለገፅታው ማማር ሲባል ነው

በአስራ አንዱ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ዙሪያ ለበርካታ ዓመታት ሲኖሩ የቆዩ ነዋሪዎች፤ ለቅርሱ ደህንነትና ለገፅታው ማማር ሲባል ሊነሱ እንደሆነ የጠቆሙት ምንጮች፤ ነዋሪዎችን በተመረጡ ሶስት ቦታዎች ላይ ለማስፈር የ80 ሚሊዬን ብር በጀት እንደተያዘ ታውቋል፡፡ በአማራ ክልል በላሊበላ ከተማ የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎች ለዘመናት ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው ሲወራረስ በቆየ አካባቢ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ለጎብኝዎች ባለመመቸቱ፣ የአካባቢው ንፅህናና ውበት አሳሳቢ ሆኖ በመገኘቱ፣ ቤቶቹ ያረጁና በርካቶችም በልመና ተግባር የተሰማሩ ስለሆኑ ለቅርሱ ደህንነት ሲባል ከስፍራው መነሳታቸው አስፈላጊ ሆኗል ተብሏል፡፡

ከመኖሪያ ስፍራቸው የሚነሱ ነዋሪዎች በከተማዋ የተመረጡ ሦስት ስፍራዎች ለማስፈር ዝግጅቱ መጠናቀቁን የጠቆሙት ምንጮች፤ ለቤት፣ ለመንገድና መሠረተ ልማት ማሟያ፤ እንዲሁም ለአርሶ አደሮች ለሚከፈል ካሳ የላሊበላ አስተዳደር ከአለም ባንክ የ80 ሚሊዬን ብር ድጋፍ ማግኘቱን ገልፀዋል፡፡

ዘንድሮ በቱሪስት መስህብነት የሚታወቁትን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ከ74 አገራት የተውጣጡ ከ35ሺ 5መቶ በላይ የውጭ አገር እና 18 ሺ የአገር ውስጥ ዜጎች እንደጎበኙት ሲገለፅ፤ ከ95 ሚሊዬን ብር በላይ ገቢ መገኘቱንም ምንጮች ጠቁመዋል፡

 

 

Read 33106 times Last modified on Saturday, 28 July 2012 15:11