Print this page
Monday, 12 October 2020 08:51

“ም/ቤቱ በትግራይ ክልላዊ መንግስት ላይ= ያሳለፈው ውሣኔ ተገቢ ነው” - ተቃዋሚዎች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 የፌደሬሽን ም/ቤት ሰሞኑን በትግራይ ክልል አስተዳደር ላይ ያሳለፈው ውሣኔ ተገቢ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራሊስት ሃይሎች ጥምረትና የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) አስታወቁ፡፡
የዛሬ ዓመት መቀሌ ውስጥ በህወሃት የተቋቋመው የፌደራሊስት ሃይሎች ጥምረትና ትዴፓ፤ የፌደሬሽን ም/ቤት በትግራይ ክልላዊ መንግስት ያሳለፈው ውሣኔ ህጋዊና ተገቢ መሆኑን የትግራይ ህዝብ ተረድቶ፣ ለውሳኔው ተግባራዊነት ተባባሪ እንዲሆንና ከፌደራል መንግስት ጐን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ፌደራል መንግስት ውሣኔውን ህዝቡን በማይጐዳ መንገድ እንዲተገብር እንዲሁም በክልሉ መንግስት ላይ ተጨማሪ ህጋዊ እርምጃዎችን እንዲወስድም የፖለቲካ ድርጅቶቹ ጠይቀዋል፡፡
“ጐጠኞችንና በህዝብ ላይ ጫና የሚፈጥሩ ቡድኖችን መንግስት በዘለቄታው ስርአት ማስያዝ አለበት” ያለው የፌደራሊስት ሃይሎች ጥምረት በቀጣይም መሰል ጠንካራ እርምጃዎች ካልተወሰዱ አርአያነቱ መልካም አይሆንም ሁሉም እየተነሳ የሰፈር ጀብደኛ መሆኑ አይቀርም” ብሏል፡፡
የትግራይ ህዝብ በጥቂት ህገወጥ አመራሮች ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ መነጠል እንደሌለበትና የፌደራል መንግስቱ ተጨማሪ እርምጃዎችን ወስዶ ህዝቡ ነፃነቱን እንዲጐናፀፍ ማድረግ ይገባል ሲሉም የትዴፓ ሊ/መንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ተናግረዋል፡፡
አረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ለሉአላዊነት በበኩሉ፤ ም/ቤት ባሳለፈው ውሣኔ ዙሪያ በስራ አስፈፃሚ ደረጃ መክሮ የደረሰበትን አቋም በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡  

Read 10623 times