Saturday, 10 October 2020 00:00

ኢትዮጵያውያን ዛሬ ዓለማቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 “ኢትዮጵያ ነበረች አለች ትኖራለች


             በተለያዩ የአለም ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትየጵያውያን “ከመስከረም 30 በኋላ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” የሚሉ አካላትን በመቃወም በዛሬው ዕለት ዓለማቀፍ ሠላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርጉ ተገለፀ፡፡
የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ከመስከረም 30 በኋላ በኢትዮጵያ ህጋዊ መንግስት እንደማይኖርና ስርአት አልበኝነት እንደሚሠፍን እየቀሰቀሱ መሆኑን የገለፁት የሠልፉ አስተባባሪዎች፤ አሁን ያለው መንግስት ሀገሪቱን እየመራ የሚቀጥልና ህጋዊ መሆኑን ለአለም ለማሳወቅ የድጋፍ ሰልፉ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡
መንግስት የሀገሪቱን ህዝቦች አንድነትና የሀገሪቱን ሉአላዊነት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላትን እየተከታተለ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ በሠላማዊ ሠልፉ ይጠየቃል ብለዋል - አስተባባሪዎቹ፡፡
ሰልፉን ዛሬ መስከረም 30 ለማካሄድ የታለመበትን ምክንያት አስተባባሪዎቹ ሲያስረዱ፤ “ጽንፈኞች” ከመስከረም 30 በኋላ ህጋዊ መንግስት እንድማይኖርና ኢትዮጵያ እንደምትፈርስ ሲቀሰቅሱ መቆየታቸውን ይህም፤ እንዳልተሳካና ኢትዮጵያ እንደምትቀጥል ለማረጋገጥ ነው ዛሬ በተመሳሳይ ቀን የሚካሄደው ብለዋል፡፡ ባለፈው ነሐሴ ወር በአሜካና አውሮፓ “ዳውን ዳውን ኢትዮጵያ” በሚል የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ለአብዛኛው “ዝምተኛ ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያን” አንገት ያስደፋ እንደነበር ያስታወሱት አስተባባሪዎቹ፤ በዛሬው ዕለት “የኢትዮጵያውያን ድምጽ” በሚል የሚደረገው ዓለማቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ኢትዮጵያን ለማክበርና ለመዘከር ያለመ ነው ብለዋል፡፡  

Read 994 times