Saturday, 31 October 2020 11:06

6ኛው ሃገራዊ ምርጫ በግንቦት ወይም በሰኔ ለማካሄድ ቦርዱ ሃሳብ አቀረበ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

 ቀጣዩ 6ኛ ሀገራዊ  ምርጫ በግንቦት መጨረሻ ላይ ወይም በሰኔ ወር እንዲካሄድ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሃሳብ አቀረበ  ።
ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ሊካሄድ ታስቦ በኮቪድ-19 ሳቢያ የተላለፈው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በመጪው ግንቦት  ወይም ሰኔ ቢካሄድ ምቹ መሆኑን ነው ቦርዱ የጠቆመው ። የእጩዎችና የመራጭ ምዝገባ በታህሳሰ ወር  ይካሄዳል ብሏል።
ቦርዱ ባቀረበው ሃሳብ፤ላይ በቀጣዩ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአንድ ዓመት በተራዘመው ምርጫ፤ ከ90 በመቶ በላይ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ የገለፀ ሲሆን በምርጫው 50 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አብዛኞቹ የፖለቲካ ድርጅቶች በበኩላቸው፤ ከምርጫው በፊት ብሄራዊ መግባባት ይቅደም እያሉ ሲሆን ቦርዱ በቅርቡ ባቀረበው ሃሳብ  ባለፉት አምስት ምርጫ ተግባራዊ የተደረገውና  በህገ መንግስቱ የተቀመጠው የአብላጫ ድምጽ የምርጫ ስርአትን አሁን ላይ መለወጥ አስቸጋሪ ነው ብሏል።

Read 4084 times Last modified on Saturday, 31 October 2020 12:48