Saturday, 31 October 2020 11:16

የሰዓሊ ምህረት ዳዊት የስዕል አውደ ርዕይ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   የእውቋ ሰዕሊ ምህረት ዳዊት የተለያዩ የስዕልና የሸክላ ስራዎች የተካተቱበት የሥዕል አውደ ርዕይ ትላንት በቦሌ ሚካኤል አካባቢ ተከፈተ።
የስዕል ኤግዚቢሽኑ ከዚህ በፊት የስዕል አውደ ርዕይ ቀርቦበት በማያውቅ አዲስ ቦታ፣ ቦሌ ሚካኤል፣ ደቡብ ግሎባል ባንክ ያለበት ህንፃ፣ አንደኛ ፎቅ ላይ ለእይታ መቅረቡን ሰዓሊዋ ለአዲስ አድማስ ተናግራለች።
”አርት የትኛውም ቦታ ላይ ለሰው ቅርብ ሆኖ መገኘት አለበት በሚል ከተለመደ ወጣ ባለ ቦታ ተከፍቷል” ብላለች - ሰዓሊዋ። የስዕልና የሸክላ ስራዎቿን ያካተተው አውደ ርዕዩ፤ ለአንድ ሳምንት ክፍት ሆኖ  እንደሚቆይም ታውቋል፡፤

Read 673 times