በደራሲ መላኩ አለማየሁ የተዘጋጀውና 8 የህፃናት ተረቶችን የያዘው “ጆሮ ቆንጣጩ” የተሰኘ የህፃናት የተረት መጽሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ።
መጽሐፉ የኢትዮጵያ ህፃናት የአገራቸውን ተረቶች እንዲያውቁና እግረ መንገዳቸውንም የንባብ ባህልን እንዲያዳብሩ በእጅጉ የሚያግዝ መሆኑን ደራሲው ገልጿል። በ32 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ45 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በጐንደርና ባህርዳር የመጽሐፍት መደብሮች ይገኛል ተብሏል።
Saturday, 31 October 2020 11:28
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና