Saturday, 31 October 2020 11:43

October አመታዊ የጡት ካንሰር ወር፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)


           ጥቂት እሳት ችላ ከተባለ እና በጊዜው እንዲጠፋ ካልተደረገ አንድ ጫካን እንደሚ ያወድም ሁሉ የጡት ካንሰርም በጊዜው ካልታከመ በመላው የሰውነት ክፍል በመ ሰራጨት ለሞት ይዳርጋል፡፡
በአላት ወይንም ቀናት ተለይተው በየአመቱ ሲከበሩ ወይንም ሲታወሱ ብዙ አስደሳች ነገሮች በሕሊና ይቀራሉ። ጭርሱንም የማይረሱ ነገሮችም በማስታወሻነት ይመዘገባሉ፡፡ እነዚህ ቀናት ግን ሁልጊዜ የሚጨፈርባቸው ወይንም በመብል መጠጥ የምናከብራቸው ወይንም የአበባ ስጦታ በመቀባበል የምናስታው ሳቸው አይሆኑም፡፡ ሌሎችም ቀናት አሉ። ሕመምንና ሕመም ተኞችን የምናስታውስባቸው ወይንም ስለአንድ ጉዳት አስቀድሞ እውቀት የምናስጨብጥባቸው፤ ንቃተ ሕሊናን የምናዳብ ርባቸው አመታዊ ቀናት በአለም አቀፍ ደረጃ ተወስነው በየአመቱ ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡ ከእነዚህኞቹ ቀናት አንዱ የአለምአቀፉ የጡት ካንሰር ቀን ነው ይላል የአለም የጤና ድርጅት WHO:: ዛሬ ማለቂያው የሆነው እ.ኤ.አ October የተባለው ወር በአለም አቀፍ ደረጃ የጡት ካንሰር ወር በሚል በተለያየ መልክ ታስቦ የሚውል ሲሆን በተለይም እ.ኤ.አ October 19 በአለም አፍ ደረጃ ንቃተ ህሊና የሚዳብርት፤ በሕመሙ ምክንያት ያለፉ የሚታወሱበት፤ ሌሎች እንዳያልፉ ትምህርት የሚሰጥበት ቀን ነው፡፡ የጡት ካንሰር ቀን ፒንክ ሪቫን ደረት ላይ በማድረግ የሚገለጽ ነው፡፡
በአጠቃላይ ካንሰር የተባለው ሕመም በማንኛውም ሰው ላይ በተለያየ የሰውነት ክፍል ሊፈጠር የሚችል በየአመቱ በአለም አቀፍ ደረጃ 9.6 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ለህልፈት የሚዳረጉበት አስከፊ በሽታ ነው፡፡ የጡት ካንሰር ደግሞ በተለይ ለሴቶች አደገኛ የሆነ በሽታ ሲሆን በሽታው አስከፊ ከተባለው ደረጃ ከመድረሱ አስቀድሞ መመርመርና በጊዜ ሕክምና በማድረግ ብዙዎች ባይፈወሱ ኖሮ ሁሉም በሽታው የያዛቸው ሴቶች ሊሞቱ እንደሚችሉ መገመት አያስ ቸግርም፡፡ ለዚህም ነው ለመላው አለም ሴቶች አስቀድማችሁ ንቁ የሚል ጥሪ እንዲሆን በየአመቱ October ሙሉ ወሩ የጡት ካንሰርን ማሰቢያ ወር ሲሆን በተለይ 19ኛው ቀን ደግሞ የጡት ካንሰርን ለመከላከል የሚያስችሉ ድርጊቶች ጎልተው በየመድረኩ የሚታዩበት እለት እንዲሆን የተወሰነው፡፡ እንደየአለም የጤና ድርጅት መረጃ በየሰላሳው ሴኮንድ በአለም ላይ በተለያዩ ሀገራት ሴቶች የጡት ካንሰር እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው ምርመራ ያደርጋሉ፡፡
አንዲት የጡት ካንሰር ይዞአት የነበረች እናት ምስክርነትዋን እንደሚከተለው ልካልናለች፡፡
‹‹….የጡት ካንሰርን በግል መመርመር ወይንም እኔ እራሴ ሰውነቴን ፈትሼ ማወቅ እንዳለብኝ ሲባል ብሰማም ምንም አድርጌ አላውቅም፡፡ አንድ ቀን ገላዬን ስታጠብ የአንደኛው ጡቴ ጫፍ ወደብብቴ ዞሮ አገኘሁት፡፡ ለአንደኛው ልጄ እየፈራሁ አማከርኩት። ዛሬ እቤት እንዳትውይ…ነይ እንዲያውም ብሎ ይዞኝ ወደሆስፒል ሄደ፡፡ ሐኪሞቹ ወዲያውኑ አፋጥነው ሕክምና ስለጀመ ሩልኝ የኬሞቴራፒ ሕክምናዬን ጨርሼ ጡቴን ኦፕራሲዮን ተደርጌ በቀጠሮ እየተመላለስኩ በመታየት ላይ ነኝ። የወደፊቱን እግዚሀር ያውቃል። እህቶቼን በሙሉ ልመክር እወዳለሁ፡፡ እባካችሁ ሐኪሞቹ እንደሚሉት እራሳችሁን አስቀድማችሁ ፈትሹ። የምትጠራጠሩት ነገር ሲኖር ፈጥናችሁ ወደሐኪ ቤት ሂዱ፡፡››
ማንኛዋም ሴት ከመስታወት ፊት ቆማ ወይንም ገላዋን በምትታጠብበት ወቅት እጆችዋን በተራ በተራ ወደላይ እየዘረጋች ጡትዋን …ዙሪያውን ያለውን አካል …በብብትዋ አካባቢ በሙሉ እየዳበሰች የተለየ በመፈተሸ የተለየ ስሜት ካላት ወደ ሐኪም ሄዳ ማማ ከር ይጠበቅባታል፡፡ አንዳንድ የተለያዩ ሁኔታዎች በጡቱ ጫፍ ላይም ሆነ በአጠቃላይ በጡቱ ላይ የምትመለከት ከሆነም ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ እድሜን ለማራዘም ይረዳል፡፡  
ይድረስ ለኢትዮያውያን ወንድሞቼ የሚል መልእክት ለባልዋ እንደጻፈች የሚነገርላት እናት ለምን ደብዳቤውን እንደጸፈች ባለቤትዋ ሲመሰክር እንዲህ ይላል፡፡
‹‹…ባለቤቴ ግልጽ ለሆነ ውይይት ሴቶችንና ወንዶችን የምታነሳሳበት ደብዳቤ ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ህብረተሰቡ የጡት ካንሰር በኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ እንዳይከሰት ለማድረግ የሚ ያስችሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችል ግንዛቤ እንዲፈጠር የምትመክርበትም ነበር…›› ይላል፡፡ ደብዳቤው የሚከተለውን ሀሳብ ይዞአል፡፡
‹‹…አምናለሁ፡፡ የጡት ካንሰርን በሚመለከት ንቃተ ህሊናን በመፍጠሩ ረገድ እና ገና ሕመሙ ሲጀምር ሕክምና ማድረግ እንደሚገባ እና ችላ ሳትሉ ክትትል ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንዶች ምርጥ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ አምናለሁ፡፡ በቅድሚያ እኛ ሴቶቹ ስለዚህ ገዳይ ስለሆነው በሽታ ምንነትና እንዴት ለሕክምናው እርምጃ መውሰድ እንደሚገባን እራሳችንን ማስተማር ይጠበቅብናል፡፡ በብዛት የሚቆጠሩ እናቶች፤ እህቶች እና ሚስቶች የጡት ካንሰርን እንዴት መከላከል እንዳለባቸው እና ስር ከመስደዱ በፊት መቼ ወደሕክምና ተቋም መሄድ እንደሚገባቸው ካለማወቅ የተነሳ ይቸገራሉ፡፡ ስለዚህም ምንም ሕመም ከመሰማቱ በፊት ወይንም በአካል ላይ ምንም ምልክት ከመታየቱ አስቀድሞ ማሞግራፊ የሚባለውን የጡት ኤክስሬይ ሕክምና ማግኘት እንዳለባቸው አምነው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው መምከር እና ማስተማር ወይንም ንቃተ ሕሊናቸውን ማዳበር ከማንኛውም ሀሳቡ ካለው ሰው ይጠበቃል፡፡ ስለዚህ ባሎች፤ ወንድሞች ወይንም አባቶች ይህ ኃላፊነት እንዳለባቸው አውቀው አጠገባቸው ያሉ ሴቶች ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ አለባቸው።›› ይላል ደብዳቤው፡፡
ከላይ ለባለቤትዋ ደብዳቤ የጻፈችው ሴት የጡት ካንሰር ታማሚ የነበረች ነገር ግን ከህመሙ የዳነች ናት፡፡ ከአስር አመት በፊት ይህንኑ ሕመም ታምማ ወደውጭ ሄዳ የታከመች እናትም የሚከተለውን ምስክር ነት ሰጥታለች፡፡
‹…እኔ በጡቴ ላይ እንደቁስል ስሜት ያለው ትንሽ ክብ ነገር ነበር የተመለከትኩት፡፡ ለባለቤቴ ሳሳየው ግን እሱ ሊቋቋመው አልቻለም፡፡ እንደ እብደት ነገር ነበር ያደረገው፡፡ እኔ ደግሞ ድንዝ ብዬ …ይድናል…ምንም አይለኝም እላለሁ፡፡ እሱ እኔን ትቶ ለካስ ወደውጭ ሄጄ የምታከምትን መንገድ እያመቻቸ ነበር፡፡ በድንገት ነበር ተነሽ ልብስሽን አዘጋጂ እንሄዳለን ያለኝ፡፡ ወዴት… ስለው ወደህክምና አለኝ፡፡ ምንም ሳልል ተከትዬ ወደ ታይላንድ ሄድኩ፡፡ ሕክምናዬን ጨርሼ… ለክትትል ግን ወደዚያ መሄድ እንደማያስፈልገኝ ተነግሮኝ መጣሁ፡፡ ባለቤቴ በወሰደው እርምጃ እነሆ ከአስር አመት በላይ እድሜዬን አርዝሜአለሁ፡፡ እኔ ባለቤቴን በጣም አከብረዋለሁ፡፡ እወደዋለሁ፡፡ ችላ ሳይል ኃላፊነቴ ነው ብሎ ስላሳከመኝ እስከአሁን አለሁ፡፡ የወደፊቱን እግዜር ያውቅልኛል…ይህ ድጋፍ ከሁሉም ወንዶች ይጠበቃል፡፡›› ብላለች፡፡
ሴቶች ብዙውን ጊዜ ለስነተዋልዶ ጤናቸው ትኩረት የማይሰጡት ከባሎቻቸው ወይንም ከቤተሰ ቦቻቸው ድጋፍ ሳይኖራቸው ሲቀር፤ የኢኮኖሚ ችግር፤ የህክምና ተቋም ርቀት፤ በላይ በላይ የተ ወለዱ ልጆች ሲኖሩ እና ተን ከባካቢ ከሌላቸው፤ሕክምና በበቂ ሁኔታ በአቅራቢያቸው አለማግ ኘት፤ ስለሕመሙ ግንዛ ቤውን ከማጣት በመሳሰሉት ምክንያቶች ነው፡፡ የጡት ካንሰ ርም ሆነ ሌሎች የመራቢያ አካላት ካንሰር ሕመሞች የሴት ወይንም የወንድ ተብለው የሚተው ሳይሆን በጋራ አንዱ ላንዱ በመተሳሰብ እርምጃ የሚወስዱበት ሕይወት እንዳትቀጠፍ ታትረው ሊሰሩ በት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
የጡት ካንሰር ሴቶችንም ሆነ ወነዶችን ሊያጠቃ የሚችል ሲሆን የወንዶቹ የለም በሚባል ደረጃ በጥቂት ወንዶች ላይ የሚከሰት ነው፡፡ የጡት ካንሰር በአለም አቀፍ ደረጃ በተለይም ሴቶችን የሚያጠቃ መሆኑ በሚደረጉ የጤና ምርመራዎች የተረጋገጠ ነው፡፡ ምንም እንኩዋን የተለያዩ ቁጥሮች በተለያዩ መረጃዎች ቢታዩም ተቀራራቢ በመሆናቸው ABC Global Aliance እንደሚለው የጡት ካንሰር በአለም አቀፍ ደረጃ በአመት እስከ 1.7 ሚሊዮን የሚደርሱ አዳዲስ ሴት ታማሚዎች ይገኛሉ ሲል እ.ኤ.አ 2012 ያወጣው መረጃ ይጠቁማል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ IARC Globocan,2008 ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ 1.38 ሚሊዮን የሚሆኑ አዳዲስ ታማሚዎች ለሕክምና የሚቀርቡ ሲሆን ወደ 458.000 የሚሆኑ ሞቶችም ተመዝግበው እንደ ነበር ይገልጻል፡፡ World cancer research Fund እንደሚለው እ.ኤ.አ 2018 ላይ ወደ ከ2/ሚ ሊዮን በላይ የሚሆኑ የጡት ካንሰር ሕመምተኞች ለህክምና ቀርበዋል፡፡
የጡት ካንሰር በአለም አቀፍ ደረጃ ባደጉትም ሆነ በማደግ ላይ ባሉት ሀገራት በሴቶች ላይ የሚታይ አስከፊ ሕመም ሲሆን ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን በዝቅተኛ እና በመካከለኛ ደረጃ በሚገኙ ሀገራት እየተለመዱ ከመጡ አንዳንድ የህይወት ልምዶች የተነሳ የጡት ካንሰር ሕመም እየሰፋ መምጣቱን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ World cancer research Fund እንዳወጣው መረጃ ለጡት ካንሰር ሕመም ምክንያቶች ከሚባሉት ውስጥ አልኮሆል መጠጣት፤ክብደቱ ከፍተኛ የሆነ ልጅ መውለድ እና የታዳጊዎች ቁመት አለመመጣጠን ከወር አበባ መቋረጥ አስቀድሞ የጡት ካንሰር እንዲከሰት ከሚያደርጉ መካከል ናቸው፡፡                         

Read 12481 times