Monday, 02 November 2020 08:26

በገበታ ለሃገር ፕሮጀክት ንግድ ባንክ የ1.1 ቢሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ አባላት፣ ማኔጅመንትና ሠራተኞች ለገበታ ለሃገር ፕሮጀክት የ1.1 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በሌላ በኩል ባንኩ ለቆጣቢ ደንበኞቹ ሽልማት ሰጥቷል።
 ባንኩ ለ9ኛ ጊዜ ባዘጋጀው የ “ይቆጥቡ ይሸለሙ” መርሃ ግብሩ 50 ያህል ሽልማቶችን ለባለ ዕድለኞች ሠጥቷል።
ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 17 በወጣው 2 የመኖሪያ አፓርታማዎችን እንዲሁም መለስተኛ የጭነት ተሸከርካሪዎች ጨምሮ በአጠቃላይ 50 ሽልማቶች ለእድለኞች ደርሰዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦርድ፣ ፕሬዝዳንትና ሰራተኞች ለገበታ ለሃገር የሚውል የ1.1 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የለገሱ ሲሆን እስካሁን ለፕሮጀክቱ ከተለገሱ የገንዘብ ድጋፎች ከፍተኛው መሆኑ ታውቋል፡፡ ባንኩ ላደረገው ልገሳም ከጠ/ሚሩ አድናቆት ተችሮታል።   

Read 4464 times