Saturday, 07 November 2020 13:00

የትምህርት ቤት መከፈት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

            ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ይጀመራል ተብሎ የነበረው የ2013 ዓ.ም የተገለፀው የመማር ማስተማር ሂደት ላተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተገለፀ።
ከአዲስ አበባ ት/ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ት/ቤቶቹ የማይከፈቱት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የመከላከያ ዝግጅት በተሟላ ሁኔታ ባለመጠናቀቃቸው ነው። በከተማዋ የሚገኙ ት/ቤቶች በ2013 ተማሪዎችን ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሚያጋልጥ ሁኔታ ዝግጅቶቻቸውን በማጠናቀቅ ጥቅምት 30/2013 ትምህርት እንደሚጀምሩ ውሳኔ ላይ ቢደርስም ት/ቤቶች ዝግጅቶቻቸውን በበቂ ሁኔታ ባለማጠናቀቃቸው ምክንያት የትምህርት ማስጀመሩ  ሂደቱ ላልተወሰነ ጊዜ  እንዲራዘም ተወስኗል። የትምህርት ከመጀመሩ በፊት በኮቪድ-19 የቀውስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂ እቅድ ላይ የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ማሟላት   አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ያለው የትምህርት ቢሮው መረጃ አስፈላጊው ዝግጅት በተሟላ ደረጃ እስከሚጠናቀቁ  ድረስ በከተማዋ ለመጀመር ታቅዶ የነበረው የገፅ ለገፅ  ትምህርት ማስጀመር መርሃ ግብር ላልተወሰነ ጊዜ  ተራዝሟል ብሏል።
ጥቅምት 16 2013 የተጀመረው የስምንተኛና አስራ ሁለተኛ  ክፍሎች የገፅ ለገፅ የክለሳ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት  ግን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቢሮው ያወጣው መረጃ አመልክቷል።


Read 727 times