Print this page
Saturday, 07 November 2020 13:49

“ከኤማሁስ ጥላ ስር” መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ ሰራዊት ዮሃንስ የተፃፈው “ከኤማሁስ ጥላ ስር ”የተሰኘውና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው ልቦለድ መፅሀፍ ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በማሪዩት አፓርትመንት ሆቴል ይመረቃል።
መፅሀፉ መቼቱን በኦሮሚያዋ የማዕድን እምብርት ሻኪሶ ላይ አድርጐ፣ በአካባቢው ባህል፣ የአኗኗር ዘይቤ፣ ባህላዊ ወርቅ አወጣጥ፣ ስለ ወርቅ አውጪዎች አመጋገብና ጨዋታ፣ እንዲሁም ስለ አካባቢው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚዳሰስ ነው ተብሏል። በምረቃው ስነ- ሥርዓት ላይ ገጣሚያን የስነ ጽሁፍ ሰዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደመው፣ ግጥምና ከመጽሀፉ የተመረጡ ታሪኮች በተጋባዥ እንግዶች እንደሚነበብ ደራሲው ሰራዊት ዮሀንስ ገልጿል። በ259 ገጽ የተቀነባበረው መፅሀፉ በ105 ብር ለገበያ ቀርቧል።


Read 10997 times