Print this page
Saturday, 07 November 2020 13:51

“ዳሪክ” የጥበብ ምሽት ነገ በአዳማ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በዳሪክ ጥበባት አዘጋጅነት የተሰናዳው “ዳሪክ የጥበብ ምሽት” ነገ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም በአዳማ (ናዝሬት) ወንጂ ማዞሪያ በሚገኘው የባ ሆቴል ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ እንደሚካሄድ የዳሪክ ጥበባት መስራች እና አዘጋጅ ተስፋ ብዙ ወርቅ ገልጿል።
በዕለቱም ገጣሚያኑ ኤሊያስ ሽታሁን፣ ኤፍሬም መኮንን (ኤፌሚክ)፣ ዳግም ደጀኔ (ሄራን)፣ ቅዱስ የገጠር ልጅ፣ ታምሩ ተመስገን፣ ማርቆስ ዘመንበረ ልዑል እና ሱራፌል ተስፋዬ የግጥም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን የስነ ልቦና አማካሪው እንደሻው ጌታቸው የሞዴሊንግ መምህርቷ ሰላም አለማየሁ (ሰሊና) የዘንደሮው ጣና ሽልማት በበጎ አድራጎቱና ሰብአዊነት ዘርፍ እጩ የነበረችው ቆንጅት ሁሴን በልዩ እንግድነት ቀርበው ስራዎቻቸውን በማቅረብ ወጣቱን ያነቃቃሉ ተብሏል። መድረኩ በዳሪክ ጥበባት መስራችና አዘጋጅ ተስፋ ብዙወርቅ  እንደሚመራ ለማወቅ ተችሏል።

Read 10907 times